በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ፋይናንስ ጽሕፈት ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ2ኛ ዙር ጥቅል ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Lessan(Feb 07, 2026)

ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር፦ 002/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ፋይናንስ ጽሕፈት ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ2ኛ ዙር ጥቅል ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች  እንድትወዳደሩ እናሳውቃለን፡

ሎት

የዕቃዎቹ አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብር

ሎት1

የእስቴሽነሪ ዕቃዎች

5,000 ብር

ሎት2

የፈርኒቸር ዕቃዎች

25,000 ብር

ሎት3

የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት

5,000 ብር

ሎት4

የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

8,000 ብር

ሎት5

የኤሌክትሮኒክስ መለዋወጫ ዕቃዎች

5,000 ብር

ሎት6

የህትመት አገልግሎቶች

5,000 ብር

ሎት7

የኤሌክትሮኒክስ ጥገና አገልግሎቶች

5,000 ብር

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የ2018 ዓም ወይም የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፡፡
  3. የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ኮፒ ከሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችል።
  4. ለሚያቀርቡት ዕቃ የጥራት ደረጃውን የሚገልጽ፣ ሥልጣን ካለው አካል የተረጋገጠ ማስረጃ ኮፒ ከሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችል።
  5. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  6. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው።
  7. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመከፈል ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 305 ቀርቦ መግዛት ይቻላል።
  8. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዋጋ የተሞላበትን የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ቢሮ ቁጥር 305 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  9. ጨረታው በ10ኛው ቀን በ11፡00 ሰዓት ታሽጎ፣ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው የመዝጊያና መክፈቻ ቀኑ የሥራ ተነካም፡ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው።
  11. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ለማይቀርብባቸው ቋሚ ዕቃዎች መሥሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሠረት ወይም (ፎቶ) ማቅረብ ይቻላል።
  12. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
  13. መሥሪያ ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. ተጫራቾች ዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ቢፈጠር ተጫራቹ ከፊት ለፊቱ መፈረም አለበት፤ ካልሆነ ግን ዋጋው ተቀባይነት አይኖረውም።
  16. የጨረታ ሰነዱ አንዱ የጨረታ የግዥ መመሪያ አካል መሆኑን ተጫራቾች ሊረዱት የሚገባ ሲሆን፣ ኦርጅናል የጨረታ ሰነዱን የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ማስገባት መመለስ ይኖርባቸዋል። ነገር ግን በጨረታ በሰነዱ ያልተካተቱ ችግሮች ቢያጋጥሙ በግዥ መመሪያ መሰረት የሚዳኝ ይሆናል፡፡
  17. የሚሞላው ዋጋ ቫትን (VAT) ያካተተ መሆን አለበት።
  18. ጨረታውን ለመወዳደር የእቃጥራት እና የዋጋ ዝቅተኛነት ግምት ውስጥ የምናስገባ ይሆናል፡፡
  19. የጨረታ ሂደቱን ለማዛባት ወይም እንቅፋት ለመፍጠር የሚሞክር ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይደረጋል።
  20. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በዋጋ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እና ራስን ከጨረታ ማግለል አይቻልም፡፡ እንዲሁም ለአንድ እቃ ለሚቀርበው ናሙና ተለዋጭ ናሙና ማቅረብ አይቻልም፡፡
  21. ከጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ፦ ከሚያደራጃቸው መሥሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ፣ ምን አይነት ምርት እንደሚያመርቱ እና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። እንዲሁም የሀገር ውስጥ ምርት ችርቻሮ ወይም ጅምላ ንግድ ከሆነ ደግሞ ከአምራች የተሰጠ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው።

ለተጨማሪ መረጃ፦ ፕላዛ ሆቴል 100 ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 305 በአካል በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 0118538953 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 04 ፋይናንስ ጽ/ቤት