Your cart is currently empty!
ሕብረት ባንክ አ.ማ. ተሽከርካሪዎች በግልፅ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል
Reporter(Feb 08, 2026)
የሐራጅ ማስታወቂያ
ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዛቸውንና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ተሽከርካሪዎች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል::
|
ተራ ቁ.
|
የተበዳሪ ስም
|
የአስያዥ ስም
|
አበዳሪው ቅርንጫፍ |
የሰሌዳ ቁጥር |
የተሽከርካሪ አይነት |
የስሪት ዘመን |
የሻንሲ ቁጥር |
የሞተር ቁጥር
|
የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ተ.ዕ.ታን ሳይጨምር)በብር |
ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ኤልሻይን ትሬዲንግ ኃ/ የተ/የግ/ማ/
|
ኤልሻይን ትሬዲንግ ኃ/ የተ/የግ/ማ/
|
መሐል አራዳ
|
አአ-03- A53273
|
አነስተኛ የሕዝብ– ኮሪያ ሀዩንዳይ
|
2014 እ.አ.አ.
|
KMHWG81R7 EU621989
|
G4KG- DA387443
|
1,530,000.00 |
የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት |
|
2 |
ኤክሶቴስማህ ትሬዲንግ የተ/የግ/ማ/
|
ኤክሶቴስማህ ትሬዲንግ የተ/የግ/ማ/
|
ገርጂ
|
አአ-03- B32696
|
የመስክ ተሸከርካሪ– ጃፓን ቶዮታ
|
2021 እ.አ.አ.
|
JTMHV02J5 04336410
|
1VD- 0583909
|
16,800,000.00 |
የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
የሐራጅ ደንቦች፡-
1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ (Hibret Bank SC) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ::ከባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም።
2 ተሽከርካሪዎችን ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከባንኩ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላል።
3. የተሽከርካሪዎች ሐራጅ የሚካሄደው የሕብረት ባንክ ኢማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ(ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው።
4. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪ እና አስያዥ ናቸው።
5. ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል::ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት።
6. ከፍ ሲል የተጠቀሱትን ተሽከርካሪዎች ለሚገዛና የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟላ ተጫራች በሚሰጠው ከፍተኛ ዋጋ ላይ ባንኩ 50%(ሃምሳ በመቶ) ብድር ያመቻቻል።
7. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል።
8. ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል::ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲቀበለው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል::በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል።
9. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች የጨረታ አሸናፊ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ይከፍላል።
10. ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. ለተጨማሪ መረጃ የሕግ አገልግሎት መምሪያ በስልክ ቁጥር 0114 70 03 15 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።