Your cart is currently empty!
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የፃግብጂ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ለወረዳው ሴ/መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸው የመነሃርያ አጥር ግንባታ በወረዳው ካፒታል በጀት፣ የመፀዳጃ ቤት እና የጣራ ውሀ ማሰባሰብ ግንባታ በዋን ዋሽ የበጀት ድጋፍ፣ አዲስ የምንጭ ማጎልበት ግንባታ ስራዎች እንዲሁም የውሃ እቃዎች በመደበኛ ካፒታል በጀት እና በሰቆጣ ዲክላሬሽን የበጀት ድጋፍ በግልፅ የጨረታ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት (ማሰራት) ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 11, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የፃግብጂ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ለወረዳው ሴ/መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸው ሎት 1 የመነሃርያ አጥር ግንባታ በወረዳው ካፒታል በጀት፣ ሎት2 የመፀዳጃ ቤት እና የጣራ ውሀ ማሰባሰብ ግንባታ በዋን ዋሽ የበጀት ድጋፍ፣ ሎት 3 አዲስ የምንጭ ማጎልበት ግንባታ ስራዎች እንዲሁም ሎት 4 የውሃ እቃዎች በመደበኛ ካፒታል በጀት እና በሰቆጣ ዲክላሬሽን የበጀት ድጋፍ በግልፅ የጨረታ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት (ማሰራት) ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን
1. በየዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)
4. የግዥ መጠኑ ከ 200,000 በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ
5. ከላይ ላሉ የግንባታ ስራዎች ከደረጃ 8 ጀምሮ እንዲሁም ለምንጭ ግንባታ ስራዎች ከአርቲዥያን ጀምሮ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ 1% በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
7. ሙሉ የስራ ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ሰነዱን ገንዘብ ጽ/ቤት ላይ መግዛት ይቻላል።
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከ4/6/2018 እስከ 18/6/2018ዓ.ም ቀናት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ሰነዱን በመግዛት የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ፃ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ19-6-2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ19-6-2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን።
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. ጨረታው ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በወረዳው ፃ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በአካል በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ።
14. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህግና ደንቦች በግዥ መመሪያ ቁጥር 2003 ተግባራዊ ይደረጋል።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ዞን የፃ/መ/ገንዘብ ጽ/ቤት
ፃታ