በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጤና ጽህፈት ቤት የሠላም ፍሬ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 11, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ሠ/ፍ/ጤ/ጣ/ግ/ጨ/002/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በአቃቂ  ቃሊቲ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የሠላም ፍሬ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን

1. የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘረትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡

1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያወጡና የተሰጣቸው ንግድ ፈቃድ 1(አንድ) ዓመት የሞላው ከሆነ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው::

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

5, ተጫራቾች ከአሁን በፊት በመንግስት ግዢዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸውን ተገልጾላቸው ግዴታቸውን የተወጡና መልካም አፈፃፀም ያላቸው እና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የግዢ መመሪያን በአግባብ የሚከተሉ እና የሚፈጽሙ::

6. በወጣው ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2:30 እስከ 6፡30 እና ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡30 4ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 45 የግዢ ክፍል በአካል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

7. መ/ቤቱ በሚገዛቸው ዕቃዎች ማለትም በጨረታ ሰነዱ ላይ በክፍል 6 ላይ የተዘረዘረትን የዕቃዎችና ተያያዥ አገልግሎቶች ዝርዝር መግለጫ ላይ ናሙና/ሳምፕል እንድታቀርቡ በተጠየቀው መሠረት የተጠየቁትን ናሙና ሳምፕል የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ቢሮ ቁጥር 45 ግዥ የስ/ሂደት እንድታስገቡ እየገለጽን ናሙና (ሳምፕል) ያልቀረበባቸው እቃዎች ውድቅ እንደሚሆኑባችሁ አውቃችሁ ለምትወዳደሩበት እቃዎች በሙሉ ናሙና(ሳምፕል) እንድታቀርቡ እያሳሰብን የምታቀርቡትን ናሙና ሳምፕል በተመለከተ ጤና ጣቢያው የራሱን ኮድ የሚስጥ በመሆኑ በምታቀርቡት ናሙና ሳምፕል ላይ የድርጅታችሁን ስም መጻፍ ወይም መለጠፍ በጥብቅ የተከለከለ ነው::

8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን እና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማርኛ መሆን ይኖርበታል፡፡

9. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ የጠቅላላ ዋጋ 2%/ሁለት ፐርሰንት/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ CPO ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡ ለእያንዳንዱ ሎት የምታቀርቡት CPO መጠን የእንደሚከተለው ይሆናል፡

1. ቋሚ ዕቃዎች 6313 – 37,492 (ሰላሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ዘጠና ሁለት ብር ብቻ) ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ መስጠት የተከለከለ ሲሆን ነገር ግን ይህ ሆኖ ቢገኝ ከጨረታ ውጪ ይሆናሉ፡፡

10. የጨረታው ዋጋ ለ2ወር ጸንቶ ይቆያል ይህም ሲሆን ገዥና ሻጭ ተስማምተው እስከ ቀጠሉ ድረስ ለ6 ወራት ድረስ በስምምነት ይቆያል፡፡

11. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በሚመለከተ አንድ ኦርድናል እንደ ኮፒ ማቅረብ አለባችሁ

12. ተጫራቾች በተሰጣቸው የዋጋ መሙያ ሠነድ ላይ ምንም ዓይነት ስፔስፊኬሽን መጨመርም ሆነ መቀነስ አይችሉም::

13. ተጫራቾች የወሰዳችሁትን የጨረታ ሰነድ ሙሉ በሙሉ ሳይገነጣጠል ተመላሽ የምታደርጉ ሲሆን በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሰነድ ጤና ጣቢያው የማይቀበልና ከውድድር ውጭ የሚያደርግ መሆኑን ይገልጻል፡፡

14. ከጥቃቅን እና አነስተኛ ወይም ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው የሚጫረቱ ተጫራቾች ከሆኑ ምን አይነት ምርት እንደሚያመርቱ እና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሀገር ውስጥ ምርት ችርቻሮ /ጅምላ ንግድ ከሆነ ደግሞ ከአምራቹ የተሰጣቸውን ፍቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል:: ካልሆነ ግን እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ በመግዛት እና የጨረታ ማስከበሪያ፣ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ::

15. የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም:: በተጨማሪም ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ሆነው ለወደፊቱም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ ይደረጋሉ፡፡ እንዲሁም ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ይወረስባቸዋል፡፡

16. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ በመለየትና በፖስታው ላይ በመግለጽ በሰም በታሽገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጤና ጣቢያው ግቢ ቢሮ ቁጥር 45 ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11:30 ይታሸግና በማግስቱ ከጠዋቱ 4:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው በሚከፈትበት ቦታ፣ ቀንና ሰዓት በራሳቸው ምከንያት ባይገኙ የጨረታ ሳጥኑ እንዲከፈት በማድረግ ውድድሩ ይካሄዳል፡፡

17. በጨረታው ላይ ሁለት እና ከሁለት በላይ የሆኑ እጩ ተወዳዳዎች በግምጥማው እኩል ውጤት ካቀረቡ አሸናፊውን ለመለየት ዕጣ የሚጣል ይሆናል፡፡

18. አሸናፊ ተጫራች የግዢ ውል እንዲፈጽም ከመ/ቤቱ ደብዳቤ ከደረሰው ከ5ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የአቅርቦት ውል ከግዢ ፈጻሚ መ/ቤቱ ጋር መፈራረም አለበት፡፡ ውል ሰጪ ፈቃደኛ ካልሆነ በቀጣይ ከመንግስት ግዢ እንዲታገድ ይደረጋል፡፡

19. የጨረታ ውጤቱ ይፋ ሆኖ አሸናፊና ተሸናፊ ተጫራቾች እንደተለዩ በማስታወቂያ ላይ ከተገለጸ በኋላ ተሸናፊ ተጫራቾች ያሲያዙትን 2% የጨረታ ማስከበሪያ የይመለስልኝ ደብዳቤ በመጻፍ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡ አሸናፊ ተጫራች ግን የውል ስምምነት እንዲፈጽም በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ከአሸነፈበት ዕቃ አገልግሎት/ ጠቅላላ ዋጋ 10% የግዢ የውል ማስከበሪያ ሲያሲዙ ቀደም ብለው ያሲያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ 2% ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

20. ገዢው መ/ቤት በጨረታ ማስታወቂያ የተጠየቀውን ዕቃ ካቀረበው መጠን ብዛት ላይ 20% ከውል በፊት ወይም ከውል በኋላ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው::

21. አቅራቢው በገባው የውል ስምምነት መሰረት የዕቃውን ዓይነት፣ መጠን እና ጥራት ጠብቆ በውሉ ላይ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ካላቀረበ የግዢ ፈጻሚ መ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ በክፍል 8 በልዩ የውል ሁኔታዎች ላይ በተገለጸው መሠረት አሸናፊ ተጫራች ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 0.01% በየቀኑ ዕቃውን እስከሚያስረከብበት ቀን ድረስ ተቀናሽ ሆኖ ለመስሪያቤቱ የጉዳት ካሳ ገቢ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም አቅራቢው ያሸነፈበትን ዕቃ ፈጽሞ ካላቀረበ ያስያዘው የውል ማስከበሪያ 10% መ/ቤቱ ይወርሳል፡፡

22. በግዢ ፈጻሚ መ/ቤት እና በአቅራቢው መካከል የተለየ ስምምነት ከሌለ በስተቀር የተያዘው የውል ማስከበሪያ ዋስትና አቅራቢው ግዴታውን ሙሉ በሙሉ እንደተወጣ ሲረጋገጥ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግለታል፡፡

23. በጨረታ ሂደቱ ላይ ጉዳት ደርሶብኛል ወይም በጨረታ ግምገማ ውጤት ላይቅር የተሰኘ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በድጋሚ እንዲታይለት የጨረታ ውጤት ይፋ ሆኖ በማስታወቂያ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን በግዢ ፈጻሚ መ/ቤት የበላይ ኃላፊ በጽሁፍ ቅሬታውን ማቅረብ በሁለት ቀናት ውስጥ መልስ እንዲያገኝ ይደረጋል፡- ሆኖም በተሰጠው ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ሳያቀርብ ቀርቶ ቀነ ገደቡ ካለፈ በኋላ የሚመጣ ቅሬታ ተቀባይነት አይኖረውም:

24. በውድድር ወቅት በአንዱ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር በአንዱ ዋጋ መሰረት እና በአሃዝና በፊደል በሚገለጽበት ወቅት ልዩነት ቢኖር በፊደል በተገለጸው መሰረት በማስተካከል ይገመግማል፡፡

25.ተጫራቾች ያቀረቡት ናሙና ሳምፕል በሚመረመርበት ወቀት በራሱ ተፈጥሮ ቢጠፋ ወይም ቢበላሽ መ/ቤቱ ካሳ አይከፍልም::

26. ያቀረቡት ናሙና የጨረታ ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 60/ስልሳ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ እንዲወስዱ ተገልጾላቸው ጠይቀው ካልወሰዱ ለመንግስት በውርስ ገቢ ይደረጋል፡፡

27. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ዕቃዎች እስከ መ/ቤቱ መጋዘን ድረስ በራሳቸው ትራንስትርት/ ወጪ በማጓጓዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማረም የሚያቀርቡት የዕቃ አይነት ተገጣጣሚ ከሆነ በራሳቸው ወጪ ገጣጥመው ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡

28. በጨረታው ሠነድ ላይ ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዩች አስመልከቶ ማብራሪያ ቢያስፈልጋችሁ በጽሁፍ ሠላም ፍሬ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 45 በአካል በመምጣት ማቅረብ /መጠየቅ / ትችላላችሁ፡፡

29.ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- አቃ/ቃ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ሠላም ፍሬ ት/ቤት አጠገብ ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 434 0351

የሠላም ፍሬ ጤና ጣቢያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *