የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦታ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል


Addis Zemen(Feb 10, 2026)

የቦታ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር:- SSNT-T600

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በዘጠኝ (9) የክልል አየር ማረፊያዎች አክሱም (የባህል ቡና፣ ሚኒማርኬት ሱቅ፣ የስጦታ እቃ መሸጫ ሱቅ የባህል አልባሳት፣ የማር መሸጫ ሱቅ፣ እና የመረጃ ዴስክ) ባህር ዳር (የመኪና ማቆሚያ፣ የስጦታ እቃ መሸጫ ሱቅ አና የመረጃ ዴስክ) ድሬዳዋ (ካፊቴሪያ አና የመረጃ ዴስክ) ጎዴ (የመኪና ማቆሚያ፣ ካፌ እና ሬስቶራንት እና የባህል ቡና) ጎንደር (የመኪና ማቆሚያ፣ ሚኒማርኬት ሱቅ፣ የስጦታ እቃ መሸጫ ሱቅ አና የመረጃ ዴስክ) ላሊበላ (የመኪና ማቆሚያ፣ ካፌ እና ሬስቶራንት፣ የባህል ቡና እና የስጦታ እቃ መሸጫ ሱቅ) ፣መቀሌ (ካፌ እና ሬስቶራንት፣ ሚኒማርኬት ሱቅ፣ እና የመረጃ ዴስክ) ሰመራ (የመኪና ማቆሚያ) ኮምቦልቻ (የሻንጣ መጠቅለያ) የሚገኙ አርባ ስድስት (46) ክፍት ቦታዎችን ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶችን ለማቅረብ ፈቃደኛ ለሆኑ ብቁ የአገልግሎት ሰጪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡

1. ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው ማንኛውም ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 04 ቀን 2018 .. ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ባሉት ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T600 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ (Deposit Slip) ቅጂውን (scan copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።

3. በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት እያንዳንዱ ጨረታ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 90 ቀናት የሚያገለግል የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ .. (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በታሸገ እና በተለየ ኤንቨሎፕ እናየጨረታ ዋስትናየሚል ጽሑፍ የተደረገበትን የጨረታ ቦንድ የያዘ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት። ከኢንሹራንስ እና ቅደመ ሁኔታ ያለው ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።

4. ተጫራቾች ህጋዊ ሰነዶቻቸውን (የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መታወቂያ እና የቫት ሰርተፊኬቶች) እና የመወዳደሪያ ፋይናንሺያል ፕሮፖዛል ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን በተለያየ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማሸግ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ በሚገኘው ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል እስከ መጋቢት 04 ቀን 2018 .. ከቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን 930 ሰዓት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ: የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

/ ሰላማዊት አባተ በስልክ ቁጥር፡ +251-11 517-4258 በመደወል መጠየቅ ይቻላል

ኢሜል: selamawita@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *