Your cart is currently empty!
የአሶሳ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኢንተርፕራይዝ የደንብ ልብሶች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 11, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት የአሶሳ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኢንተርፕራይዝ የ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤታችን ሠራተኞች የቦርድ አመራሮች አገልግሎት የሚውል የደንብ ልብሶች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ጨረታውን መወዳደር የምትፈልጉ፡
- በዘርፉ የተሰማሩበት የአቅራቢነት ምስክር ወርቀት፣ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የፌዴራል መንግስት በዘርፉ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ሰለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ እና የውል ስምምነት 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በኢፌዴሪ የውሃ ሚኒስቴር ቢሮ ቁጥር 211 ድረስ ቀርቦ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 30,000 ብር (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚሸጡበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በኢፌዴሪ የውሃ ሚኒስቴር ቢሮ ቁጥር ድረስ በመምጣት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን ተጫራቾች በራሳቸው ፍቃድ ባይገኙ የጨረታው ሂደት አይስተጓጎልም።
- ተጫራቾች በሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን በሙሉ ወይም በከፊል በመሙላት መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን እቃዎች እስከ አሶሳ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኢንተርፕራይዝ ንብረት ክፍል ማስረከብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ አሸናፊ ሊያደረጋቸው የሚችልና የዕቃው ነጠላ ዋጋ ያልተጋነነ መሆን አለበት።
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰርዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-ለእያንዳንዱ ዕቃ ወይም ጨርቅ ናሙና መቅረብ አለበት፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ ወይም ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0917856765 /0917178915 ይደውሉ።
የሠራተኞች ደንብ ልብስ አይነትና መግለጫ የያዘ ዘንጠረዥ
|
ተ.ቁ |
የእቃው ዝርዝር መግለጫ |
መለኪያ
|
ዓይነት
|
ብዛት
|
ጠ/ድ
|
የአንዱ ዋጋ |
ምርመራ |
ጠቅላላ ዋጋ |
ምርመራ |
||
|
ብር |
ሣ |
ብር |
ሣ |
||||||||
|
1 |
አንደኛ ደረጃ ቴትረን/ካኪ ቴትረን |
ሜትር |
|
1008 |
|
|
|
|
|
|
|
|
2 |
አንደኛ ደረጃ ነጭ ቴትረን ሞዴል 6000 ጨርቅ |
ሜትር |
ነጭ ቴትረን |
63 |
|
|
|
|
|
|
|
|
3 |
የወንድ እጅጌ ሙሉ ሸሚዝ 100% የማያንስ ኮተን በትልቁ፣ በመካከለኛውና በትንሹ |
ቁጥር |
ከ100% የማያንስ ኮተን የሆነ |
288 |
|
|
|
|
|
|
|
|
4 |
ጥራት ያለው የወንድ አጭር /ጉርድ ቆዳ ጫማ በጥንድ |
በጥንድ |
|
138 |
|
|
|
|
|
|
|
|
5 |
ጥራት ያለው የወንድ አጭር /ቡትስ ቆዳ ጫማ በጥንድ |
በጥንድ |
|
140 |
|
|
|
|
|
|
|
|
6 |
ጥራት ያለው የሴት አጭር ቆዳ ጫማ |
በጥንድ |
|
60 |
|
|
|
|
|
|
|
|
7 |
ጥራት ያለው ሙሉ የስፖርት ቱታ |
በቁጥር |
|
31 |
|
|
|
|
|
|
|
|
8 |
ጥራት ያለው የዝናብ ልብስ |
በቁጥር |
|
9 |
|
|
|
|
|
|
|
|
9 |
ጥራት ያለው የወንድ ቶርሽን ጫማ |
በጥንድ |
|
31 |
|
|
|
|
|
|
|
|
10 |
ካፖርት |
በቁጥር |
|
19 |
|
|
|
|
|
|
|
የአሶሳ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኢንተርፕራይዝ