Addis Zemen (Apr 22, 2026)
ዕቃዎችን ለመሸጥ የመጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ጅግጅጋ/ስተአ/001/2018
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ዕቃዎች (ላፕቶፕ እና ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ የማባዣ ማሽኖች፣ ቴሌቪዝኖች፣የመኪና መለዋወጫዎች፣ የተለያዩ የውሃ እቃዎች፣ የግንባታ እቃዎች እና ሌሎችም ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ባመጣው የዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡–
1) ተጫራቾች የተዘጋጀውን የሽያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ጅግጅጋ በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ፋይናንስ ቢሮ በመገኘት እና ክፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከሚያዝያ 14/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 27/2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።
2) በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት/Refugees and Returnees Service /በሚል የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ / CPO/ የባንክ ዋስትና /Bank Gurantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
3) ማንኛውም ተጫራች ከሚያዝያ 14 እስከ ሚያዝያ 27/2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ጅግጅጋ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ በመገኘት ዕቃዎቹን መመልከት/መጎብኘት/ ይችላል።
4) ጨረታው ጅግጅጋ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ የሚካሄድ ሲሆን የጨረታው ሳጥን ሚያዝያ 27 ከቀኑ 8፡30 ታሽጎ በዕለቱ ሚያዝያ 27 ከቀኑ 9፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
5) የጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋሰትና በ3 ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
6) ተጨራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ አለባቸው።
7) በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጨራች ለጨረታው ማስከበርያ ያስያዘው ሲፒኦ ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ገቢ በማድረግ የተሻለውን አማራጭ የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8) አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9) ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– +251 929 361 915, +251 934 335 039 ወይም +251 915 741 708 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት