Addis Zemen (Apr 22, 2026)
የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ
አይናጌ ሕፃናት እና ቤተሰብ ልማት ድርጅት በኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በዳግም ምዝገባ ቁጥር 1544 ተመዝግቦ የሚገኝ በኢትዮጵያ ነዋሪዎች ድርጅት በማዕከላዊ አትዮጵያ በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ በተለያዩ የልማት ተግባራትን እያከናወነ የሚገኝ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነዉ።
ስለሆነም እ.ኤ.አ ከሐምሌ 2025 እስከ ሰኔ 30,2026 ድረስ ለ1 ዓመት አጠቃላይ ገቢና ወጪዉን እንዲሁም የፕሮግራም አፈጻጸም ጥራቱን በዉጭ ኦዲተር ማስመርመር የሚፈለግ ሲሆን ከአሸናፊዉ የኦዲት ድርጅት ጋር ለ3 ዓመታት ዉል ገብቶ ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም ማንኛዉም የአዲት ድርጅቶች ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን መስፈርቶች መሟላት የሚችሉ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በጨረታዉ መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በቀጣይ የስራ ቀን ተከፍቶ አሸናፊው ይፋ ይደረጋል።
- የኦዲተርነት የፍቃድ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
- የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
- ከፌደራል ወይም ከክልል ኦዲት መ/ቤት ለበጀት ዓመቱ የታደሰ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- ካሁን በፊት ባከናወኑዋቸው የኦዲት ስራዎች የመልካም ስራ አፈጻጸም ድርጅቶች ሰለመስራታቸዉ የሚያሳይ መረጃ ማቅረብ የሚችል።
በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች መረጃውን እና የምትሰሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ቢሯችን ድረስ በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን።
ማሳሰቢያ፡–
የኦዲት ድርጅቱ ለሚልከዉ ባለሙያ ማንኛውንም የምግብ የአልጋ፤ የትራንስፖርት እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን በራሱ ይሽፍናል።
አድራሻ ስልጤ ዞን ቅበት ከተማ ከቦዜ ት/ቤት ፊት ለፊት (ከአዲስ አበባ ሆሳዕና በሚወስደው መንገድ ከቡታጅራ ከተማ 12 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ)
ስልክ ቁጥር 0913 381 437 / 0916 040 327
አይናጌ ሕፃናት እና ቤተሰብ ልማት ድርጅት