Addis Zemen (Apr 23, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 004/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ እና በዙሪያዋ ለሚገኙ ነዋሪዎች ለሁሉም ክ/ከተሞች ጤና መድህን ተጠቃሚዎች ለፌደራል ጤና መድህን ተጠቃሚዎች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ጥራታቸውና ፈዋሽነታቸው የተረጋገጡ መድሀኒቶች እና የሕክምና መገልገያዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ በ53 መድሀኒት ቤቶች የዱቤ /credit እና የጥሬ ገንዘብ/ cash ሽያጭ አገልግሎት እየሰጠ ያለ የመንግስት የልማት ድርጅት ነው። ስለሆነም ድርጅቱ ከነማ ፋርማሲ የመድሃኒት እና የህክምና መገልገያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
መስፈርቱን የምታሟሉና ብቁ የሆናችሁ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
1. በንግድ ዘርፍ ወይም በመስኩ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው እና የቲን ማስረጃዎች።
2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለ 7 ተከታታይ የስራ ቀናት (ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ ) ጉለሌ ከ/ከተማ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS / ኤስ ኤም ኤስ ኤስ / ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
3. ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 8ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚቻል ሲሆን 4፡30 ሰዓት የጨረታው ሳጥን የሚታሸግ ስለሆነ አርፍዶ የሚመጣ ተቀባይነት የለውም። በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን በድርጅቱ ግዥ ዳሬክቶሬት ክፍል 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 የሚከፈት ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡– ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡– ከፒያሳ ወደ አዲሱ ገበያ በሚዎስደው መንገድ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS / ኤስ ኤም ኤስ ኤስ / ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403፤
የስራ ሰአት፡– ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 827-9123
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት