Addis Zemen (Apr 24, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጌዴኦ ዞን የኮቾሬ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለኮቾሬ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት እና ለፍ/ገነት ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የሚውል ሞተር ሳይክሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስስሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች የሚያሟሱ ተጫራቾችን ይጋብዛል።
1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑ
4. የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
5. የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
6. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ 50,000/ሃምሳ ሺህ/ ብር ማስያዝ የሚችሉ
7. የጨረታ ሠነድ በማይመለስ 200/ ሁለት መቶ / ብር መግዛት የሚችሉ
8. ከአሰሪ መስሪያ ቤት ጋር በሚገባዉ ውል መሠረት በጨረታ ያሸነፉትን ሞተር ሳይክሎችን ማስረከብ የሚችሉ፡-
9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ መሆኑን የሚያውቅ፡-
ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሠነድ በኮቾሬ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 01 ከ16/08/2018 ዓ/ም እስከ 10/09/2018 ዓ/ም ድረስ እየተሸጠ ቆይቶ በ16ኛው የሥራ ቀን ላይ በ11/09/2018 ዓ/ም ዕለተ ማክሰኞ ከረፋዱ 05፡00 ሰዓት ላይ የመጫረቻ ሠነድ ኦርጂናሉንና የማይመለስ አንድ ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እናት/ፖስታ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ገብቶ በዕለቱ ከረፋዱ 05፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታዉ በግልጽ ይከፈታል፡፡
ለበለጠ መረጃ
046-366-0433/+251916920261 /+251916634937
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በጌዴኦ ዞን የኮቶሬ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት