አንበሳ ባንክ አ.ማ. ከዚህ በፊት ይጠቀምባቸው የነበሩ ያገለገሉ ኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች፣ የቢሮ ማሽኖች እና የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

አንበሳ ባንክ አ.ማ. ከዚህ በፊት ይጠቀምባቸው የነበሩ ያገለገሉ ኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች፣ የቢሮ ማሽኖች እና የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Apr 26, 2026)

ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ ማስታወቂያ

ቁጥር 001 2018 ግል ጨረታ

አንበሳ ባንክ አማ ከዚህ በፊት ይጠቀምባቸው የነበሩ የለገሉ ኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች፣ የቢሮ ማሽኖች እና የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ ባለብት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሬት ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 200 – 11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 200 – 6፡00 ሰዓት ብር 230 (ሁለት መቶ ሰላሳ ብር ከባንኩ ዋና /ቤት ስር በሚገኘው የካ ቅርንጫፍ በመክፈል ከሚያዝያ 21 ቀን 2016 . እስከ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓም ከቀኑ 800 ድረስ መግዛት ይችላሉ

የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት በሰንጠረዥ በተጠቀሰው መሰረት ይሆናል።

ተ.ቁ

የእቃው አይነት

የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች

ግንቦት 10 ቀን 2016 .. ከቀኑ 800

ግንቦት 10 ቀን 2016 .. ከቀኑ 830

 

2

የቢሮ ማሽኖች

3

የቢሮ ፈርኒቸሮች

 

2. ከጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም

3. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4 ወይም 25% በባንክ በተረጋገጠ በክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ CPO/ በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ስም አስርተው በታሸገ ኢንቬሎፕ ከነሙሉ አድራሻው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ማንኛውንም ተጫራች የሚገዛውን የንብረት አይነት በመጥቀስ በባንኩ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ሞልቶ በታሸገ ኢንቨሎፕ ፖስታ በማድረግ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል

5 የጨረታው መወዳደሪያ ሰነድ ግልፅ እና ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን ይኖርበታል። ስርዝ ድልዝ የተደረገበት ዋጋ ከሆነ በመረቻ ሰነዱ ላይ ፈራሚ አካል ፓራፍ ኢንሺያል ፊርማ ማድረግ ይኖርበታል

6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በአሃዝ እና በፊደል እንዲሁም ከቫት በፊት እና በኃላ መሆኑ መግለፅ አለባቸው።

7. ተጫራቾች ንብረቶቹን ከገንቦት 6 እና 7 ቀን 2018 . ከቀኑ 7:30~ 10፡00 አና ግንቦት 8 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 2:30 – 530 ቀደም ብሎ ቀጠሮ በማስያዝ ቃሊቲ በሚገኘው የአንበሳ ኢንሹራንስ ሪከቨሪ ጊቢ ውስጥ፣ ከደራርቱ አደባባይ ወደ አያት ጣፎ በሚወስደው መንገድ ከለሚ ኡራ ፖሊስ ጣቢያ ከፍ ብሎ እና ቦሌ መድኃኒዓለም ማፊ ሞል አጠገብ በሚገኘው የባንካችን ህንፃ ቤዝመንት ወለል ማየት ይቻላል።

8. ጨረታው 22 አካባቢ የቀድሞ ዘሪሁን ህንፃ ፊት ለፊት ሌክስ ፕላዛ 4 ፎቅ ላይ በሚገኘው በአንበሳ ባንክ ዋና /ቤት 4 ወለል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

9 የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፈበትን ሙሉ ክፍያ በመፈፀም ያስያዙትን ሲፒኦ (CPO) መውሰድ የሚችል ሲሆን ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 3 (ሶስት) የስራ ቀናት ጊዜ ውስጥ ይመለስላቸዋል።

10 አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ 3 የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ለባንኩ ከፍለው ንብረቱን 3 ቀናት ውስጥ መረከብና ማንሳት ይኖርባቸዋል

11. በተባለው ጊዜ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉም ሆነ ገቢ አድርገው ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ /ሲፒ / ለባንኩ ገቢ ሆኖ ንብረቱ እንደ አስፈላጊነቱ ለሁለተኛ አሸናፊ ወይም በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።

12. አሸናፊ ተጫራቾች ለተጫረቱበት ንብረት ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላሉ።

13. ስለእያንዳንዱ ንብረት ዝርዝር እና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አማ ዋናው /ቤት ግዥ እና ፋሲሊቲስ ማኔጅመንት መምሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011 636-2064/ 09 19 76 81 34/ 09 13 58 12 40/ 09 23 78 92 51 ማግኘት ይቻላል።

14. ባንኩ ስለንብረቶቹ አሻሻጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ሽያጩን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አንበሳ ባንክ . ዋና መ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *