Addis Zemen (May 05, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በብላቴ ዙሪያ ወረዳ፣ ጠጢቻ ወረዳ እና ቦና ዙሪያ ወረዳ የኮብልስቶንና የጎርፍ መውረጃ ቦይ ግንባታ በ2018 በጀት ዓመት ለማሰራት በብላቴ ዙርያ ወረዳ መዉረጃ ቦይ ግንባታ በ2018 በጅት ዓመት ለማሰራት በብላቴ ዙርያ ወረዳ በሌላ ከተማ Lot 1/18 የጎርፍ መውረጃ ቦይ ግንባታ & Lot 2/18 በጠጢቻ ወረዳ ጠጢቻ ከተማ የጎርፍ መውረጃ ቦይ ግንባታ እና ወረዳ በቦና ከተማ ቀሪ የኮብልስቶን ማንጠፍ ስራ ህጋዊ ተጫራቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
1. ለሚሰራ የኮብልስቶንና የጎርፍ መውረጃ ቦይ ግንባታ ሥራ ደረጃቸው GC-5 ተቋራጮች 2018 በጀት ዓመት ፍቃዳቸው ያደሱና የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ አግባብነት ካለው መንግሥት ተቋም (በፌደራል እና በሲዳማ ክልል) የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ( VAT) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
2. አስፈላጊ የግንባታ ማቴሪያሎች የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶች በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መስራትና ማጠናቀቅ አለባቸው።
3. በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ፕሮጀክት ሰርተው ለማስረክብ ክአሰሪና ከሚመለከታቸው መስራያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በሥራ ወቅት ከኣሰሪ መ/ቤት ወይም ከአማካሪ መ/ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ኮንትራክተሮች የጨረታ ሰነድ መግዛት ሆነ መወዳደር አይችሉም።
4. በከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ የስራ ውል ገብቶ ያላስረክበ ተቋራጭ የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም
5. በገባዉ ዉል መሰረት ፕሮጀክት ሰርቶ ያስረከበ ተቋራጭና የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል።
6. ድርጅቱ ለውድድር ያቀረበው ብቃት ( ቴክኒክ መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና ( ኦርጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው ይህ ተጣርተው ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ድርጅቱ ከውድድር ውጪ ይሆናል።
7. የጨረታ ማስከበርያ (bid security) ብር 200,000/ ሁለት መቶ ሺህ ብር) የክፍያ ማዘዣ(CPO) ብቻ ከማጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ
8. ተጫራቾች በተጫራቾች መመሪያና ደንብ መሠረት ሕጋዊ ፍቃዳቸውንና ተ.እ.ታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሠርተፊኬት ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 20 (ሀያ ) ተከታታይ ቀናት 1000.00 /ኣንድ ሺህ ብር/በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ግዥ/ፋይናንስ በመክፈል ሰነዱ መውሰድ ይችላሉ።
9. አንድ ተጫራች ከአንድ ሎት በላይ መወዳደርም ሆነ የጨረታ ሠነዱን መግዛት አይችልም።
10. ማንኛውም ተጫራቾች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት በራሳቸው ወጪ አይቶ ማረጋገጥ አለባቸው።
11. የጨረታ ሰነድ በተጫራቶች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ ( CPO) ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) ሁለት ሁለት ኮፒዎች እንዲሁም የቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) ሁለት ሁለት ኮፒዎች በተለያየ ኢቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተክተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቅያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ግዥ/ፋይ/አስተዳደር ክፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባችዋል።
12. ጨረታው ተጫራቾች ውይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግተው ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ይከፈታል የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መክፈት አያግደውም።
13. ጨረታው ላይ ባለው ጠቅላላ ዋጋ ከአስር ፐርሰንት(10%) በላይ የዋጋ ቅናሽ (Rebate) የተደረገ ከሆነ ድርጅቱ ቀጥታ ከጨረታ ወድድር ውጪ ይሆናል።
14. አሠሪ መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
15. የጨረታው መግቢያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሰዓት ይሆናል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ
በስልክ ቁጥር፡- 046 212 4356
በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ