Reporter (May 06, 2026)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ፀደይ ባንክ አማ ለአቶ እንግዳየሁ ፋንታሁን ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዘውን በአብክመ ክልል በእንጅባራ ከተማ 02 ቀበሌ የካርታ ቁጥር 77/2010 በአቶ አክሊሉ መኮንን ያለው ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን 1 ክታር ስፋት ያለው ሲራሚክ ፋብሪካ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- የቤቱ የጨረታ መነሻ ዋጋ ግምት ብር 51,094,692,50 (አምሳ አንድ ሚሊየን ዘጠና አራት ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና ሁለት ብር ከ50 ሳንቲም) ነው።
- ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ) በፀደይ ባንክ ኢማ ስም በማሰራት ለጨረታ መስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታው የሚሳተፈው በሕግ ሰውነት ያገኘ ሰው ከሆነ የድርጅቱን መመስረቻ ጽሑፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ፤ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበትን የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ሕጋዊ ውክልና ማቅረብ ይኖርበታል።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጨረታ ያሸነፈውን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። አሸናፊው በ15 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ያሆናል።
- በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ይመለስላቸዋል።
- የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% ይከፈልበታል እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማንኛውንም ወጭዎች ይሸፍናል። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረው የሊዝ ክፍያ ገዡ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
- ተጫራቾች ቤቱን በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ።
- ጨረታው ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 በእንጅባራ ከተማ በፀደይ ባንክ አማ እንጅባራ ዲስትሪክት ቢሮ ላይ ይደረጋል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር
09 18 77 98 25