ዋንዛ ፈርኒሺንግ ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ለእንጨት ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ጣውላዎችን በግልፅ ጨረታ ግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ዋንዛ ፈርኒሺንግ ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ለእንጨት ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ጣውላዎችን በግልፅ ጨረታ ግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 08, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ዋ/ፈ/ኢ/ጣግጨ /19/2018

ዋንዛ ፈርኒሺንግ ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ከታች የተዘረዘሩትን ለእንጨት ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ጣውላዎችን በግልፅ ጨረታ ግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ

የባህር ዛፍ ምሰሶ ቁመት

ዝርዝር መግለጫ/Specification

1

Local Pine (የፈረንጅ ጥድ፤ ሻሸመኔ)

 

ቁመት፡ 4፡00 ሜትር

ስፋት፡ 20-30 ሴሜ

ውፍረት፡ 2.5-5 ሴሜ

2

Australi Solid Wood

 

ቁመት፡ 4.00 ሜትር

ስፋት፡ ከ20-30 ሴሜ

ውፍረት፡ 2.5-5 ሴሜ

 በመሆኑም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሱ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፤

  • ተጫራቾች በዘርፉ መወዳደር የሚያስችል የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TN no) እና ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ከጨረታ መወዳደሪያ ኦሪጂናል ሰነድ ጋር በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ዋንዛ ፈርኒሺንግ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ወይም Wanza Furnishing industry Private Limited Company ስም ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሰሚት ፔፕሲ ፋብሪካ በስተጀርባ በሚገኘው በድርጅቱ አንደኛ ፎቅ የግዥ መምሪያ ክፍል ውስጥ በመቅረብ የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፤ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የሎካ ፓይነስ እና አውስትራሊያ – አይነት በግልፅ ለይተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ እስከ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከታች በተገለፀው አድራሻ ጠዋት 4፡00 ድረስ ማስገባት ይጠቅባቸዋል።
  • ጨረታ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡30 ከታች በተገለጸው አድራሻና ቦታ ይከፈታል፤ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • የጨረታ ሰነዱ የሚገኝበት አድራሻ፡- ዋናው መ/ቤት አዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክ/ከ ወረዳ 10 የቤት ቁጥር አዲስ ሰሚት ከፔፕሲ ፋብሪካ በስተጀርባ በሚገኘው የዋንዛ ፈርኒሺንግ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር አንደኛ ፎቅ ግዥ መምሪያ ቢሮ::

ስልክ ቁጥር 0911-926283

ዋንዛ ፈርኒሺንግ ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *