በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የሚውል የተለያዩ የደንብ ልብስ አይነቶችን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የሚውል የተለያዩ የደንብ ልብስ አይነቶችን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 09, 2026)

የተስያዩ የደንብ ልብስ ቁሳቁሶች ግዥ

ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 422/18

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የሚውል የተለያዩ የደንብ ልብስ አይነቶችን ግዥ በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተዘረዘረው መሰረት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

/

የዕቃው አይነት

ብዛት

የጨረታ ማስከበሪያ

የሚታሸግበ ሰዓት

ሰነዱ የሚገኝበት ቦታ

1

የተለያዩ ብዛት ያላቸው ደንብ ልብስ ዕቃዎች

ብዛታቸውን በሚሸጠው ሰነድ ውስጥ ይገኛል

50,000

16ኛው ቀን 400 ታሽጎ በዕለቱ 430 ይከፈታል

///ቢሮ ዲላ መምህራን ኮሌጅ ግቢ

በንግድ ስራ ዘርፍ የታደሰ ፍቃድ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውና የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃዎች ያላቸውና የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል፡፡
  • በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ያሲያዙበትን ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች በቢሮ የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው ተከታታይ እስከ 16 ቀን 1130 ድረስ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በዲላ ከተማ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ መምህራን ኮሌጅ ግቢ ከሚገኘው የግብርና ቢሮ ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ከፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ በመሙላት ይህ የጨረታ የቴክኒካልና ፋይናሻል ኦርጅናልና ኮፒ የማጫረቻ ሰነዶች በአንድ ፖስታ በማዘጋጀት 16 ኛው ቀን 400 ሰዓት በቢሮ ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል፡፡ እንዲሁም የጨረታው ሳጥን 400 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 410 ተጫራቾች (ተወካዮቻቸው) በተገኙበት በቢሮው የግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ከፍል ይከፈታል፡፡
  • 200,000 ሺህ ብር በላይ ለሆነ ግዥዎች ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  • ቢሮው በቀረበው ጨረታ ላይ ካሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት የግዥውን 20% ፐርሰንት መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል፡፡
  • የጨረታው ሳጥን መክፈቻ 16ኛው ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣይ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • ሁለት ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት ዋጋቸው እኩል በሚሆንበት ወቅት በእጣ የሚለይ ይሆናል፡፡
  • ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ 046-131–0134 ይጠቀሙ፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ግብርና ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *