Addis Zemen (May 10, 2026)
የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ- አንቀፅ 1 መሰረት በ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር የከተማ መሬት በልዩ የሊዝ ጨረታ ለሆቴል/7/፣ ለሞልና አፓርታማ/10/ በድምሩ /17/አስራ ሰባት የሚሆኑ ቦታዎችን በልዩ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
1. መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በአማራ ቴሌቪዥን ጨረታው እንደሚጀምር ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 አስር የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 2000/ሁለት ሺህ/ በመክፈል ቀበሌ 08 ከአዲሉ መሬት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 310 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ የጨረታ ሰነድ መሸጥ ከጀመረበት ቀን አንስቶ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 11፡ዐዐ ሰዓት ብቻ በቢሮ ቁጥር 30 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይሆናል፡፡
3. ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
4. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጥዋቱ በ4፡00 ሰዓት ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበትን ቦታ በተመለከተ በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
5. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በመምሪያው የውስጥ ማስታወቂያ መለጠፊያ ሰሌዳ እና በBahirdar City Communication የፊስ ቡክ ገፅ ማግኘት ይቻላል፡፡
6. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ
ባህር ዳር