Addis Zemen (May 11, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
አፈ/ከሳሽ እነ ዳንኤል አምበሉ አፈ/ተከሳሽ እነ ዮሐንስ መስፍን መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክርክር ጉዳይ ስም በደ/ማ/ከተማ ቀበሌ 02 ሰፈር 2 የቤት ቁጥር 455 የሆነ በ500 ካ/ሜትር ቦታ ላይ የተሰራ መኖሪያ ቤት ከነ ሰርቪሱ ካርታና ፕላን ያልተሰራለት አዋሳኙ በምስራቅ ወ/ሮ ምንትዋብ ብዙነህ ፣ በምዕራብ ወ/ሮ የሻለም ልመንህ ፣ሰሜን መንገድ፣ ደቡብ ታሪኩ ወርቅነህ የሚያዋስኑት ሰርቪስ ቤት ግምት ብር 85,530/ ሰማኒያ አምስት ሺህ አምስት መቶ ሰላሳ ብር/ ፤ ዋናው ቤት ግምት ብር 126,724.50/ አንድ መቶ ሀያ ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሀያ አራት ብር ከ50/100 ሳንቲም/፣ የመሬት የቀጠና ዋጋ 1,167,875/አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ስልሳ ሰባት ሺህ ስምንት መቶ ሰባ አምስት ብር/ አጠቃላይ መነሻ ዋጋ 1,380,129.50/አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰማኒያ ሺህ አንድ መቶ ሀያ ዘጠኝ ብር ከ50/100 ሳንቲም/ የሚሸጥ ቤቱና ሰርቪሱ ተነጣጥሎ የማይከፈል የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአንድ ወር በአየር ላይ ውሎ ጨረታው ሰኔ 05 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ በጨረታ ይሸጣል።
ስለሆነም ከላይ የተጠቀሰውን መኖሪያ ቤት ከነሰርቪሱ መግዛት የሚፈልግ ተጫራች በመጀመሪያ ደረጃ ጨረታ መነሻ ዋጋውን 25% በCPO አስይዘው ያስያዙበትን ደረሰኝ ወይም /ሪሲት/ ለሀራጅ ባይ በእለቱ በማስያዝ መጫረት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ አሸናፊ መሆኑ እንደታወቀለት ደግሞ የሽያጩን ጠቅላላ ገንዘብ 75% የማስያዝ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን ካላስያዙ ግን ለጨረታ ማስፈፀሚያ የወጡ ልዩ ልዩ ወጭዎች ተቀንሶ ቀሪው ለመንግስት ገቢ የሚሆን መሆኑን እንገልፃለን።
በደ/ማርቆስ ከ/ወ/ፍ/ቤት