Addis Zemen (May 12, 2026)
የሃይቤድ፣ ሎውቤድ እና የጭነት መኪና ከነተሳቢው የአገልግሎት ግዥ ለመፈፀም የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢግ.ሥ.ኮ/ብግጨ/13/2018
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2018 በጀት ዓመት የሃይቤድ፣ ሎውቤድ እና የጭነት መኪና ከነተሳቢው አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት (Specification) መሰረት አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር ለመከፈላችሁ ማስረጃ፡ የቫት ተመዝጋቢ፤ ቲን፤ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ በሚገኘው ፋፋ የምግብ ኢማ ጀርባ በሚገኘውየኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ) በሲፒኦ ወይም በባንከ ጋራንቲ (unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። የጨረታ ዋጋ ለ30 (ሰላሳ) ቀናት የጸና መሆን ይኖርበታል። ጨረታው ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነሥርዓት ይከናወናል።
ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡–
ስልክ +251 911 984 467 ወይም +251 913 080 126
ፋክስ 0114-421 312
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ