አብክመ ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በሰንበቴ ከተማ አስተዳደር የሰንበቴ ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት ጠቅላላ ስፋት 170 ካሬ ሜትር የሆነ አንድ ቦታ ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ ሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

አብክመ ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በሰንበቴ ከተማ አስተዳደር የሰንበቴ ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት ጠቅላላ ስፋት 170 ካሬ ሜትር የሆነ አንድ ቦታ ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ ሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል


Addis Zemen (May 12, 2026)

የመጀመሪያ ዙር የመሬት ሽያጭ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

አብክመ ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በሰንበቴ ከተማ አስተዳደር የሰንበቴ ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሠረት በሰንበቴ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ጠቅላላ ስፋት 170 ካሬ ሜትር የሆነ አንድ ቦታ ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ ሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ፍቃደኛ ተጫራቾች

1.1 የጨረታውን ሰነድ በሰንበቴ ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት በመሬት ልማትና ማኔጅመንት ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።

1.2 ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ድረስ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎቹን ሁኔታ በማየት ዋጋማቅረብ ይችላሉ።

1.3 ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቶች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው ስፔስፊኬሽን /Specification/ መሠረት መሆን ይኖርበታል።

1.4 ተጫራቶች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከማገኘው ውጤት 5 በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ5 ከመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል።

1.5 ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ሲፒኦ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ በሰንበቴ ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት በመሬት ልማትና ማኔጅመንት ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ከ3/09/2018 እስከ 15/09/2018 ዓ ም ኩቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

1.6 ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ15/09/2018 ዓ ም 11፡00 ሰዓት ይሆናል።

1.7 ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ18/09/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት በሰንበቴ ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ ቤት አዳራሽ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

1.8 ቦታውን ለመጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ለሽያጭ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት በሰንበቴ ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት በሚመድባቸው አስጎብኝዎች ቦታዎቹን መመልከት ይችላሉ።

1.9 የአካባቢውን ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ መነሻ ዋጋ እና ሌሎች የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሠረት በማድረግ በሰንበቴ ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከት ይችላሉ።

1.10 መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 033 118 0376 ወይም 09 31 96 91 82 መጠየቅ ይችላሉ፤
አብክመ ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በሰንበቴ ከተማ አስተዳደር የሰንበቴ ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *