በላይአብ ሞተርስ ኃ.የተ.የግል ማኅበር የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በላይአብ ሞተርስ ኃ.የተ.የግል ማኅበር የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (May 12, 2026)

የመለዋወጫ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

በላይአብ ሞተርስ ኃ.የተ.የግል ማኅበር የተለያዩ የተሸከርካሪ መለዋወጫዎችን ማለትም-

የሲኖ ትራክ SINO Truck)፤ የኒሳን ዩዲ (Nissan UD)፤ የኪያ (KIA) ፤ የፉቶን ዳምፕ ትሪከ(Foton Dump Truck) ፎርክፈት(Forclift) ፤ የሎደር (Loader) ፤የኤክስካቫተር(Excavator) የሪዮት ኮንትሮል (Riot Control) የዳምፐር(Damper)፤የዜድ ኤን ኤ ፒክ አፕ(ZNA pick up)፤ ሪች(Richy) የቢሾፍቱ ፒክ አፕ(Bishoftu pick Up)፤የፎቶን ፒከ አፕ(foton pick up)፤የፎርላንድ (Forland)፤ የፋዎ ቤላ(FAW BELLA)፤የኦቲንግ(Oting)፤ የፎቶን ሚኒ ባስ (Foton mini Bus)፤ ሙዳን ባስ(Mudan Bus) ፤ኤፍሲ.አር (FSR)፤ ጋርቤጅቲፐር(Garbage Tipper)፤ ካኒባላይዝ (Canibalize) ኪያ (KWA) እና ዎኪንግ ትራክተር (Walking Tractor) መለዋወጫዎችን(Spare parts) በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። እቃዎቹ አዲስ አበባ እና አዳማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ይገኛሉ።

ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

1) የጫረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመግዛት ዋጋቸውን በመሙላት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።

2) ጨረታው የሚቆየው ጋዜጣው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ሲሆን በ11ኛው ቀን 4፡00 ተከፍቶ 4፡30 ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሳሪስ ቀይመስቀል ወስጥ በሚገኘው በላይአብ ሞተርስ ይከፈታል፡፡

3) ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የተለያዩ መለዋወጫ እቃዎች ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

4) ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ድርጅቱ ባወጣው የመነሻ ዋጋ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5) ተጫራቾች ሰነድ ከገዙ በኋላ ቃሊቲ ብሔራዊ ት/ቤት ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በመቅረብ የእቃዎቹን ናሙና በአካል ማየት ይችላሉ፡፡

6) አሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከፍሎ በ15 ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡

7) ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8) ማንኛውም ተጫራች የሚፈልገውን የመለዋወጫ ብዛት በተናጠል መጫረት ይችላል፡፡

9) ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

ከላይ በተዘረዘሩት መስፈርት ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች ሰነዱን ሳሪስ ካዲስኮ ዋና መስሪያቤት የበላይአብ ሞተርስ ግቢ ዉስጥ መውሰድ ይችላሉ፡፡

አድራሻ

በላይአብ ሞተርስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሞባይል፡- 0966 21 51 83/84

ስልክ፡- 0114 343691

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በላይአብ ሞተርስ ኃ.የተ.የግል ማኅበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *