የሆሣዕና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ለሚያሰራው የጂ+ 2 ሞዴል የማኀበረሰብ ፋርማሲ እና ዲያግኖስቲክ ላብራቶሪ ህንጻ እንዲሁም ደረቅ መጸዳጃ ቤት ግንባታ የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሆሣዕና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ለሚያሰራው የጂ+ 2 ሞዴል የማኀበረሰብ ፋርማሲ እና ዲያግኖስቲክ ላብራቶሪ ህንጻ እንዲሁም ደረቅ መጸዳጃ ቤት ግንባታ የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (May 31, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ ኮድ-004

የሆሣዕና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ለሚያሰራው የጂ+ 2 ሞዴል የማኀበረሰብ ፋርማሲ እና ዲያግኖስቲክ ላብራቶሪ ህንጻ ንዲሁም ደረቅ መጸዳጃ ቤት ግንባታ የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት

  • ደረጃቸው BC-6/GC-7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ፣የንግድ ምዝገባ ፈቃድ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት፣የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል የጨረታ ሰነዱን ከሆሣዕና ጤና ሣይንስ ኮሌጁ ግዥ ፋይ//አስተዳደር ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 25ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ባለፈቃዱ ወይም ሕጋዊ ተወካዩ እንድ ኮፒ የሰነድ ማስረጃ በማስያዝ መግዛት ይችላል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኮሌጁ ስም 200,000/ ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional bank guarantee letter ) ከፋይናንሻል ሰነድ ጋር በፖስታ በሰም አሽገውና ማኅተም በማድረግ ፈርመው ማቅረብ አለባቸው
  • ተጫራቾች አስፈላጊውን ዕቃና ሠራተኛ አቅርበው ሥራውን የሚሠሩበትን የፋይናንሻል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጂናል ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዶችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም አራቱንም ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሸጐና የኘሮጀክቱን ስም ጠቅሶ የቴከኒካል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጂናል ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ ሰነዶች እንዲሁም ኦርጂናል ቴክኒካል ሀሳብ የያዘ ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስት በማድረግ አራቱንም የቴክኒካል ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሽጐና ሁለቱንም የቴክኒካል እንዲሁም የፋይናንሻል ፖስታዎች በአንድ ማጠቃለያ እናት ፖስታ በማድረግ የኘሮጀክቱን ስም ጠቅሶ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 26ኛው ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነዶች ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጪ ያደርጋል፡፡ የአገልግሎት ዋጋው በሰነዱ ላይ በተዘጋጀው ቦታ በአሃዝና በፊደል መሞላት ይኖርባቸዋል፡፡ ኦርጂናል የቴክኒካል ሃሣብ የያዘ ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) በየመጠይቁ ባዶ ቦታዎች ተሞልቶ ተፈርሞና ማኀተም ተደርጎ ታሽጐ መመለስ አለበት፡፡ የቴኒካል ሃሣብ የያዘውን ሰነድ (Bidder certification of compliance) አለመመለስ ከውድድር ውጪ ያደርጋል፡፡
  • ጨረታው 26ኛው ቀን 430 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ ግዥ /አስተዳደር ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 12 ሦስተኛ/3/ ፎቅ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 26ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል ፡፡

ማሳሰቢያ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ልል መንግሥት የመንግሥት የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ተፈጻሚ ይሆናል

  • ማንኛውም ተጫራች ከወቅቱ ገበያ ዋጋ በታች ያቀረበ እንደሆነ አሰሪው /ቤት ውል ለመግባት አይገደድም
  • ማንኛውም ተጫራች በመንግሥት ኤሌክትሮኒክስ ግዥ ( EGP) የተመዘገበ መሆን አለበት
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0913 568 248 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል

ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የሆሣዕና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *