የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የትራንስፖርት አገልግሎት አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የትራንስፖርት አገልግሎት አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል


Reporter (May 31, 2026)

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ

የጨረታ ቁጥር 07/18

ድርጅታችን የገባውን ሽቀጣ ሸቀጥ፣ ስር፤ ስሚንቶ እና የኢንዱስትሪ ጨዉ መነሻውን ለሸቀጣ ሸቀጥ አ/አበባ ከሚገነዉ ርጅቱ መጋዘኖች፤ ለስኳር ከሁሉም የስኳር ኢንዱስትሪ ፋብሪካዎች እና አ/አበባ ከሚገኘው መጋዘኖቹ፣ ለሚንቶ ከሁሉም የስሚንቶ ፋብሪካዎች እና የኢንዱስትሪ ጨው ከዲቼቶ ቢ፤ኦዳር፣ ዬ እና ሀነፍ ጭው ማምረቻ ከሱማሌ ክልል ኣፍሬራ ዞን ሀርገሌ ኦ ጨው አቅራቢ ማህበራት እና ከአፋር ክልል አፍዴራ ጨው አቅራቢ ማህበራት በኢትዮጵያ መድህኒትና ቁጥጥር ባለስልጣን ስር ከሚገኙት መጋዘኖች የኢንዱስትሪ ጨው አ/አበባን ጨምሮ ለተለያዩ የድርጅቱ ቅፍ መ/ቤቶች የተለያዩ የአርማታ ብረቶች ከቢሾፍቱ እና ከዱከም ብረት ፋብሪካዎች አ/ አበባን ጨምሮ ለተለያዩ በክልል ወደ ሚገኙት የድርጅቱ ቅ/ፎች ለማጓጓዝ በግልፅ ጨረታ የትራንስፖርት አገልግሎት አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል::

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶቹን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መካፈል የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን::

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግዴ ሥራ ፈቃድ፣የብቃት ማረጋገጫ ታክስ ክሊራንስ ሠረተፍኬት እና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠረተፍኬት ያላቸው መሆን ይገባቸዋል::
  2.  ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር በመክፈል ፒያሳ ቢስ መብራት አካባቢ /አትክልት ተራ/ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስርያ ቤት ከሎጀስቲክስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ::
  3. ተጫራቾች ለሸቀጣ ሸቀጥ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) ለስኳር ተጫራቾች ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ) ለሲሚንቶ ተጫራቾች ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ) እና ለኢንዱስትሪ ጨው ብር 300,000 (ሶስት መቶ ሺ) ለብረት ብር 300,000.00(ሶስት መቶ ሺህ ብር)በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO)ብቻ ከትራንስፖርት ታሪፍና ከብቃት ማረጋገጫ ማስረጃዎች ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል::
  4. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውንና ከላይ የተጠቀሱ ህጋዊ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እና በአንድ ፖስታ በማሸግ ሰኔ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባችዋል::
  5. ጨረታው ሰኔ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡10 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
  6. ተጫራቾች በጨረታው መመሪያ ላይ የተገለፀውን ደንብና ግዴታ በሙሉ የመፈፀም ግዴታ አለባቸው::

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-126-22-50


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *