በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት በወረዳ 04 ስር የሚገኘው ጀሞ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የክፍል በሮች በአዲስ መስራት፣ የሽንት ቤት በር፣ የተማሪ ዴስክ ጥገና፣ መስታወት ጥገና፣ ቴራዞ ወለል ንጣፍ ስራ፣ ጅብሰም ቦርድ፣ ሴራሚክ ንጣፍ ስራ እና ግድግዳ የቀለም ቅብ ስራ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 18, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ጀሞ 01/2018

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት /ቤት በወረዳ 04 ስር የሚገኘው ጀሞ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጥገና ስራዎች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

.

የስራው ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የብር መጠን

1

የክፍል በሮች በአዲስ መስራት፣ የሽንት ቤት በር፣ የተማሪ ዴስክ ጥገና መስታወት ጥገና

15000

2

ቴራዞ ወለል ንጣፍ ስራ፣ ጅብሰም ቦርድ፣ ሴራሚክ ንጣፍ ስራ ግድግዳ የቀለም ቅብ ስራ

15000

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
  2. የአቅራቢዎች የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
  3. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከፋይናንስና ግዢ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 4 መውሰድ ይችላሉ
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሰንጠረዡ ስር በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ኦሪጅናል አና ኮፒ ብሎ በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው የስራ ቀን 400 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከቀረበው አጭር መግለጫ (specification) ውጪ በመሰረዝ ወይም በማሻሻል ማቅረብ እና በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት አይፈቀድም
  6. ተጫራቾች ደረጃ 7 እና ደረጃ 8 ሕንፃ ስራ ተቋራጮች መሆን አለባቸው
  7. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ የጠቅላላ ዋጋውን የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ያስይዛሉ።
  8.  የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 430 ሰዓት በትምህርት ቤቱ ላይብረሪ ይከፈታል። ነገር ግን የሚከፈትበት ቀን ካላንደር የሚዘጋው ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል።
  9. ማንኛውም ተጫራች ሰነድ ገዝቶ መጫረት የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማሰራት አና አሸናፊም ሲሆን የውል ማስከበሪያ የማስያዝ ግዴታ አለበት
  10. /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • አድራሻችን፡ከአየር ጤና ወደ ዓለም ባንክ በሚወስደው መንገድ ከወረዳ 04 ትንሽ ከፍ ብሎ

ስልክ፡ 011835-30-56/011827-66-98 ደውለው ይጠይቁ።

በኮ///ከተማ //ቤት

የጀሞ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ /ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *