Your cart is currently empty!
ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አ.ማ. የተለያዩ የማሽነሪ መለዋወጫ ዕቃዎች መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በጨረታ ሰነዱ ላይ ለተዘረዘሩት የተለያዩ የማሽነሪ መለዋወጫ ዕቃዎች አጠቃላይ መመሪያዎች እና ግዴታዎች፡-
- ጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ደንበኞች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሃያ አምስት ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማቅረብ በጨረታ ሰነድ ቅጽ ላይ በመሙላትና ለጨረታ ማስከበሪያም ያቀረቡትን ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በ ሲ.ፒ.ኦ ብቻ በማስያዝ በድርጅቱ የመለዋወጫ ዕቃዎች ኦፕሬሽን ዲቪዥን ክፍል ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- በዚህ የግዢ ጨረታ የሚቀርቡ ሰነዶች በሙሉ በአማርኛ ወይም በእንግሊዝኛ ቋንቋ መጻፍ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለመግዛት የወሰኑበትን ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር ለእያንዳንዱ መለዋወጫ ዕቃ መለያ ቁጥር በተናጥል መጥቀስይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የሚፈልጉትን .የመለዋወጫ አይነት በመለየት በጥቅል ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ ገንዘብ ተቀባዮች ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ከተጠቀሰው ጊዜ በኋላ ዘግይተው የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
- ጨረታው የጨረታ ሰነዱን ማስገቢያ ጊዜ ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የሰራተኞች ክበብ ውስጥ ይከፈታል።
- የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በማስታወቂያ ከተገለጸ ቀን አንስቶ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ ዕሴት ታክስን ጨምሮ ክፍያ መፈጸም ይኖርባቸዋል።
- በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ከፍያ ፈጽመው ያሸነፉበትን ዕቃዎች የማያነሱ ከሆነ በእቃዎቹ ላይ ለሚደርሰው ጉዳት ድርጅቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
- የጨረታ ተሸናፊዎች ዝርዝር በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለጨረታው ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ. ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 011 442 1133/0929 16 90 44
ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አ.ማ.