Your cart is currently empty!
ኬ.ኤ.ኤም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በጨረታ ቁጥር 006ያገ/2017 በድርጅቱ ቅርንጫፍ መ/ቤት መከኒሳ ሮያል ሴራሚክ አፓርትመንት ቅጥር ግቢ ዉስጥ የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ እንዲሁም ሳይሸጡ ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ ካሬያቸዉ አነስተኛ የሆኑ ሴራሚክ ዕቃዎች፤ በጉዳት የተወገዱ የሴራሚክ እና ሳኒተሪ(Damage) ዕቃዎች፤ የተበታተኑ ሞዛይኮች፤ ከኮንስትራክሽን የተመለሱ ብረታ ብረቶችን፤ መስታውቶችን፤ ቆርቆሮዎችን፤ አሮጌ የከባድ ተሽከርካሪዎች ሸራዎች እና፤ የተለያዩ የመታጠቢያ ቤት አክሠሠሪዎችን እና ሌሎችንም ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
2merkato.com(Aug 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 006ያገ/2017
ቀን ነሃሴ 18, 2017 ዓ.ም
ድርጅታችን ኬ.ኤ.ኤም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በጨረታ ቁጥር006ያገ / 2017 በድርጅቱ ቅርንጫፍ መ/ቤት መከኒሳ ሮያል ሴራሚክ አፓርትመንት ቅጥር ግቢ ዉስጥ የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ እንዲሁም ሳይሸጡ ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ ካሬያቸዉ አነስተኛ የሆኑ ሴራሚክ ዕቃዎች፤ በጉዳት የተወገዱ የሴራሚክ እና ሳኒተሪ(Damage) ዕቃዎች፤ የተበታተኑ ሞዛይኮች፤ ከኮንስትራክሽን የተመለሱ ብረታ ብረቶችን፤ መስታውቶችን፤ ቆርቆሮዎችን፤ አሮጌ የከባድ ተሸከርካሪዎች ሸራዎች እና፤ የተለያዩ የመታጠቢያ ቤት አክሠሠሪዎችን እና ሌሎችንም ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ስለ አጠቃላይ የጨረታ ሁኔታ ይረዱ ዘንድ ተፈጻሚ የሚሆኑ ደንቦችን፣ ጠቅላላ ማብራሪያና አፈጻጸም ሂደቶች በተመለከተ ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለጹ ሲሆን ተወዳዳሪዎች የጨረታ መስፈርቱ የሚጠይቀውን መወዳደሪያ ነጥቦች በማሟላት ፋይናንሻል ፕሮፖዛል (ዋጋ ማቅረቢያችሁን) እንድታቀርቡ እያሳወቅን፤ በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ፡-
1. የጨረታ ማስከሪያ /Bid Bond/ ብር 50,000/ አምሣ ሺህ/ ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ / CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
2. የጨረታ ሰነዱ አዲስ አበባ ን/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 02 በጀርመን አደባባይ ምስራቅ ፀሐይ ቅድስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው ሮያል ሴራሚክ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 201 የማይመለስ 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በሪፖረተር ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል(የዋጋ ማቅረቢያ) ሰነድ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ/CPO/ በአንድ ላይ በማድረግ እና በጥንቃቄ በማሸግ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀን ነሃሴ 27, 2017 ዓ.ም ድረስ ከላይ በተጠቀሰዉ አድራሻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ጨረታዉ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
4. ዝርዝር የጨረታ መመሪያው ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለፀ ስለሆነ ማንኛውም ተጫራች በጥንቃቄ በማንበብ ዋጋቸውን በጨረታ መመሪያው መሰረት መሙላት አለባቸው፡፡
5. ለጨረታ የወጡ ዝርዝር ዕቃዎች ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ሰነዱን እና መታወቂያቸውን /ውክልና/ በመያዝ ን/ላ/ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጀርመን አደባባይ ምስራቀ ፀሀይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው ሮያል ሴራሚክ ግቢ ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት መጎብኘት ይችላሉ፡፡
6. ድርጅቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር
09 11 523 393 /09 11 667 378 ይደውሉ
ኬ ኤ ኤም ኃ/ የተ /የግል ማህበር አዲስ አበባ