በአራዳ ክ/ከተማ የመስከረም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን የመምህራን እና ሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ የቤተ ሙከራ እቃዎች፣ አጋዥ መጽሐፍት፣ የማባዣ ቀለም፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ የስፖርት መምህራን የሀገር ውስጥ ሸራ ጫማ፣ የስፖርት መምህራን ቱታ፣ የሴቶችና ወንዶች ቆዳና ቡትስ የፕላስቲክ ጫማ፣ የህትመት ሥራዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የላፕቶፕ፣ ዴስክቶፕና ፕሪንተር ግዥ፣ ልዩ ልዩ የጥገና እቃዎችና መሳሪያዎች፣ የኮምፒውተር፣ የፎቶ ኮፒ፣ የማባዣ ማሽን እና የፕሪንተር ጥገና የሚያስፈልገውን ዕቃ ጨምሮ፣ የፈርኒቸር ምርቶች ግዥ፣ የሠራተኛ የደንብ ልብስ ስፌት የእጅ ዋጋ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማስጠገን ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 23, 2025)

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 001/2018

በአራዳ ክ/ከተማ የመስከረም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን የመምህራን እና ሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ የቤተ ሙከራ እቃዎች ፣ አጋዥ መጽሐፍት፣ የማባዣ ቀለም ፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ፣ የስፖርት መምህራን የሀገር ውስጥ ሸራ ጫማ ፣ የስፖርት መምህራን ቱታ ፣ የሴቶችና ወንዶች ቆዳና ቡትስ የፕላስት ጫማ፣ የህትመት ሥራዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የላቭቶፕ፣ ዴስክቶፕና ፕሪንተር ግዥ፣ ልዩ ልዩ የጥገና እቃዎችና መሳሪያዎች የኮምፒውተር፣ የፎቶ ኮፒ፣ የማባዣ ማሽን እና የፕሪንተር ጥገና የሚያስፈልገውን ዕቃ ጨምሮ፣ የፈርኒቸር ምርቶች ግዥ፣ የሠራተኛ የደንብ ልብስ ስፌት የእጅ ዋጋ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡

በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  2. የመንግስት ግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ያላቸው፡፡
  3. የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ተጫራቾች በታሸገ ኤንቨሎፕ የገዙትን ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡
  5. ተጫራቾች የመምህራን እና ሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ አላቂ ቢሮ እቃዎች፣ የጽሕፈት መሳሪያዎች ፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች የስፖርት መምህራን የአገር ውስጥ ሸራ ጫማ እና ቱታ የሴቶችና ወንዶች ቆዳ ጫማ ፣ ቡትስ ጫማ የፕላስትክ ፣ የህትመት ሥራዎች ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ልዩ የጥገና እቃዎች፣ ልዩ መሳሪያዎች የኮምፒውተር፣ የፎቶ ኮፒ፣ የማባዣ ማሽን እና የፕሪንተር ጥገና፣ ፣ የላቭቶፕ፣ ዴስክቶፕና ፕሪንተር ግዥ፣ የፈርኒቸር ምርቶች ግዥ የሠራተኛ የደንብ ልብስ ስፌት የእጅ ዋጋ የሚያስፈልገውን ዕቃ ጨምሮ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰጠገንና ለመግዛት ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማግኘት ይችላሉ።
  6. የጨረታ ሰነዶቻቸውን ዝርዝር ተፅፎ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 3,000.00 /ሦስት ሺህ ብር/ በማስያዝ በመስከረም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 5 ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 እና ከ7-30-11፡00 ሰዓት ድረስ ከመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. አሸናፊ ተጫራቾች ካሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ጨረታው በወጣ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል።
  9. ሙሉ ከገዙ ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  10. በጨረታወ ይ ተንተርሶ ዋጋ መጨመር አይቻልም፡፡
  11. ያቀረቡበት ረጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡
  12. ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  13. ጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት እራሳቸው አምርተው ገበያ የሚያቀረቡት ዕቃ ወይም ምርት ካልሆነ በስተቀር የተዘጋጁ ዕቃዎችን ገዝተው ካመጡ የሚወዳደሩበት እንደማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ መግዛትና እና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  14. ተጫራቾች ስርዝ ድልዝ የማይነበብ ሰነድ ጨረታ ላይ ያልተነበበ የዋጋ ማቅረቢያ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ 
  15. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው እንዲሁም መ/ቤቱ ዕቃዎችን 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ የሚችል መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ – / 011 868-1356/57
አድራሻ ፡- ግቢ ገብርኤል በስተጀርባ ባዕታ ክሊኒክ አጠገብ
በአዲስ አበባ ከተማ በአራዳ ክ/ ከተማ የመስከረም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት