Your cart is currently empty!
በጉ/ክ/ከ/ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችና አልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 23, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በጉ/ክ/ከ/ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ለ2018 በጀት ዓመት በፑሉ ስር ለሚገኙ ጽ/ቤቶች የተለያዩ ዕቃዎችና አልግሎቶች በአጠቃላይ 13 ሎቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የድንኳን ኪራይ
- ሎት 2 ዲጄና ዲኮር ኪራይ
- ሎት 3 የሕትመት ስራዎች
- ሎት 4 የቦቴ ውሃ አቅርቦት
- ሎት 5 የኮምፒውተር ጥገና ሎት ሎት
- ሎት 6 የመኪና ኪራይ አገልግሎቶች
- ሎት 7 የደንብ ልብስ ዕቃዎች
- ሎት 8 የደንብ ልብስ ስፌት
- ሎት 9 የፅህፈት መሳሪያዎች
- ሎት 10 የፅዳት እቃዎች
- ሎት 11 የጥገና እቃዎች
- ሎት 12 የመኪና እቃዎች
- ሎት 13 ቋሚ የሙዚቃ መሳሪያዎች እቃዎች
1. ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን አድራሻቸውንና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማስፈር ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ጨረታ ፖስታ ላይ ለየትኛው አገልግሎት እንደሚወዳደሩ በግልፅ ለይተው መጻፍ አለባቸው።
3. ተጫራቾች ድረ ገፅ (ዌብ ሳይት) ላይ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ እንዳላቸው የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም አስተዳደሩ ባወጣው ጨረታ ላይ ከውል በፊት የዕቃውን ብዛት 20% መጨመርና መቀነስ ይችላል እንዲሁም ከውል በኃላ ደግሞ 25% የዋጋውን መጨመር ይችላል።
4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም ተጫራቾች ለተወዳደሩባቸዉ 1 እና 4 ሎቶች ናሙና ማስገባት አለባቸው።
5. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው አገልግሎቶች ወይም ዕቃዎች በሙሉ መስሪያ ቤቱ ቴክኒክ ኮሚቴ ደረጃቸውን የጠበቁ ስለመሆናቸው ይገመግማሉ።
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫት ያካተተ መሆኑን ወይም ዋጋው ከቫት ውጪ መሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው ይህ ባይሆን ዋጋው ቫት ያካተተ ተደርጐ ይወሰዳል።
7. ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ሎት 1 5,000 /አምስት ሺ ብር/ ሎት 2 10,000 /አስር ሺ ብር/ ሎት 3 10,000 /አስር ሺ ብር/ ሎት 4 10,000 (አስር ሺ ብር)፣ሎት 5 5,000 (አምስት ሺ ብር) ሎት 6 10,000 (አስር ሺ ብር) ሎት 7 10,000/አስር ሺህ ብር/ ሎት 8 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ሎት 9 20,000/ሃያ ሺህ ብር/ ሎት 10 15,000/አስራ አምስት ሺህ ብር/ ሎት 11 10,000/አስር ሺህ ብር/ ሎት 12 10,000 /አስር ሺህ ብር/ እና ሎት 13 20,000/ሃያ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ በጉ/ከ/ከ/ፐ/ሰ/ የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት ከሂ ቡድን ስም በባንከ በተመሰከረ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርበታል። ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ሎት ወይም ስነድ በመከፈል በመንግስት የስራ ሰዓት ጉለሌ ከፍለ ከተማ ፐ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ቢሮ 6ኛ ፎቅ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
8. የጨረታ ሰነዶች በሙሉ በኢንቨሎፕ ታሽገው ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት ለየብቻው በማድረግና በማያያዝ ማህተማቸውን በፖስታዎች ላይ በማኖር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
9. የካፒታል መጠናቸው ከብር 100,000 መቶ ሺ ብር/ በላይ የሆኑ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
10. የጨረታው ጊዜ የሚያበቃው በ10ኛው ቀን በ11.30 ሰዓት ታሽጐ በሚቀጥለው የስራ ቀን 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት የሚከፈት ይሆናል።
11. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
12. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናል።
13. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
14. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት ጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል ይህ ባይሆን ግን ከጨረታ ይሰረዛሉ።
15. ተጫራቾች በንግድ ፈቃዳቸው በስተጀርባ ላይ የተዘረዘሩትን የንግድ ዘርፍ አይነቶች ኮፒ አድርገው ማቅረብ አለባቸው የተጫራቾች ማህተምና የንግድ ፈቃዳቸው እንዲሁም የደረሰኛቸው ስያሜ አንድ አይነት መሆን ይኖርበታል።
16. በጨረታ መወዳደሪያ የሚቀርብ ዋጋ ለስድስት ወር ፀንቶ ይቆያል።
17. ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ከመ/ቤታችን ጋር ውል ማስከበሪያ ላሸነፉባቸው አገልግሎት ወይም ዕቃዎች የጠቅላላ ዋጋውን 10% ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ባይሆን ግን በጨረታ ያስያዙት /ሲፒኦ/ በቀጥታ ለመንግስት ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛሉ።
18. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት በእያንዳንዱ ዋጋ መሙያ ፎርማት ላይ የሚያስገቡትን ዋጋ መሙላት አለባቸው።
19. ተጫራች አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ወጪ መ/ቤታችን ወይም በሚፈለግበት ቦታ ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት።
20. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የአገልግሎት ብዛት ቀንሶ ወይም ጨምሮ ከአሸናፊው ድርጅት የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0118-12-51-78 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።
በጉ/ክ/ከ/ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን