Your cart is currently empty!
የአዲስ አበባ ሒልተን ኃ/የተ/የግ ማህበር ንብረትነቱ የልማትና ሆቴል ማህበር የሆኑ አገልግለሎት የሰጡ ቴሌቪዠኖችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Aug 24, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2025
የአዲስ አበባ ሒልተን ኃ/የተ/የግ ማህበር ንብረትነቱ የልማትና ሆቴል ማህበር (ኢማ) የሆኑ አገልግለሎት የሰጡ ቴሌቪዠኖችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
- ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን ፎርም ከአዲስ አበባ ሒልተን ኢንተርናሽናል ሂሳብ ክፍል የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብቻ ብር) በመክፈል መውሰድ ይቻላል::
- ለጨረታ የሚቀርብ ማንኛውም ተወዳዳሪ ህጋዊ ፈቃድ ያለው ሆኖ ፈቃዱም በ2017 ዓ. ም. የታደሰ መሆን ይኖርበታል::
- ቴሌቪዠኖቹን ከነሀሴ 19 ቀን እስከ ነሀሴ 22 ቀን 2017 ዓ. ም. ከጠዋቱ 3፡30 እስከ 6፡00 ብቻ የጨረታ ሰነዱን እየገዙ ማየት ይቻላል:: ነገር ግን ሁሉም ተጫራጮች በተገኙበት መነሻ ሰዓት 4፡00 ሰዓት ብቻ በመሆኑ ከ4፡00 ሰዓት ቦኃላ ዘግይቶ የሚመጣ ተጫራች እንደማንቀበል በቅድሚያ እናሳውቃለን ::
- ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ ነሀሴ 23 እና ነሀሴ 26 ቀን 2017 ዓ. ም. በሥራ ሰዓት ብቻ ሒልተን አዲሰ አበባ ዳይሬክተር ኦፍ ፋይናንስ ቢሮ ማሰገባት ይኖርባቸዋል:: ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዋጋ 10% /አስር በመቶ/ የጨረታ ማስከበሪያ/ ቢድ ቦንድ / በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ./ ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: ሲ.ፒ.ኦ. ያልቀረበበት እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ የሌለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም/ከጨረታው ውጭ ይሆናል/::
- ጨረታው ነሀሴ 27 ቀን 2017 ዓ. ም. ከጠዋቱ በአራት ሰዓት ተኩል (4፡30) ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ሒልተን የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል::
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- አሸናፊውን ካሳወቅን ቀን ጀምሮ በ5 ቀን ውስጥ ገንዘቡን ከፍሎ እቃውን በሙሉ ማንሳት አለበት::
ሒልተን አዲስ አበባ