Your cart is currently empty!
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 27, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ 001/2018
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም የሚመለከታቸው ድርጅቶች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት መስፈርቱን የምታሟሉ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ሎት 1 የደንብ ልብስ፣
- ሎት 2 ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፣
- ሎት 3 የፅዳት ዕቃዎች
- ሎት 4 የፕላንት ማሽነሪና ለመሣሪያ/ኤሌክትሮኒክስ/መግዣ
- ሎት 5 የፈርኒቸር ዕቃዎች፣
- ሎት 6 የህትመት ስራዎች፣
- ሎት 7 ትራንስፖርት አገልግሎት፣
- ሎት8. የመስተንግዶ
- ሎት 9 የልብስ ስፌት፣
- ሎት 10 ለፕላንት ማሽነሪ ኤሌክትሮኒክስ /ጥገና
- ሎት 11 የፈርኒቸር ጥገና፣
- ሎት 12 የኪራይ ዕቃዎች
- ሎት 13 የመኪና ጎማ እና የመኪና እቃዎች፣
- ሎት 14 የጉልበት ስራ በጨረታ መሳተፍ ለምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባችሁ፡-
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃቸውንና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆኑ የምስክር ወረቀትና ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤
2. ተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ህጋዊ ደረሰኝ ያላቸው መሆን አለባቸው።
3. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 1 የደንብ ልብስ 10,000 /አስር ሺህ/ ብር፣ ሎት 2. ሌሎች አላቂ ዕቃዎች 10,000 /አስር ሺህ/ ብር፣ ሎት 3 የፅዳት ዕቃዎች 10,000 /አስር ሺህ/ ብር፣ ሎት4 ለፕላንት ማሽነሪና መሣሪያ /ኤሌክትሮኒክስ/ መግዣ 10,000 /አስር ሺህ/ብር፣ ሎት 5.የፈርኒቸር ዕቃዎች 10,000 /አስር ሺህ/ብር፣ ሎት 6. የህትመት ስራዎች 5,000 /አምስት ሺህ/ብር፣ ሎት 7 ትራንስፖርት አገልግሎት 5,000 /አምስት ሺህ/ ብር፣ ሎት8. የመስተንግዶ 5.000 /አምስት ሺህ/ብር፣ ሎት 9. የልብስ ስፌት2,000 /ሁለት ሺህ/ብር፣ ሎት 10. ለፕላንት ማሽነሪ /ኤሌክትሮኒክስ/ ጥገና 2,000 /ሁለት ሺህ/ብር፣ ሎት 11 የፈርኒቸር ጥገና 2,000 /ሁለት ሺህ/ብር፣ ሎት 12. የኪራይ ዕቃዎች 5,000 /አምስት ሺህ/ ብር፣ ሎት 13.የመኪና ጎማ እና የመኪና እቃዎች ግዥ 5,000 /አምስት ሺህ/ብር ሎት14.የጉልበት ስራ ካደራጀቸው ወረዳ ደብዳቤ የቀረበ ዋስትና መሆን አለበት። ከሎት 1 እስከ ሎት 13 ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን እና በተባለው መሰረት በባንክ የተመሰከረለት/ሲፒኦ/ የተከፈለበት በአንዱ ከዋናው ዋጋ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ።
4. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰአት እስከ ቀኑ አስራ አንድ /11፡00/ድረስ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 02 በማቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
5. ተጫራቾች በእያንዳንዱ እቃ የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር በመግለጽ ፖስታ ሰነዱን በኦርጂናልና ኮፒ በድርጅቱ ክብ ማህተም ማድረግና ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
6, ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰአት ላይ ሳጥኑ ይታሸጋል፤ ስለዚህ ሁሉም ተጫራቾች ሰነዳቸውን አስገብተው ማጠናቀቅ አለባቸው።
7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች ዋጋ ሰነድ ሲያቀርቡ ኦርጂናልና ደረጃውን የጠበቀ ናሙና በጽ/ቤቱ ግዥ ቢሮ ማድረግ አለባቸው።
8. ተጫራቾች ያሸነፏቸውን እቃዎች ተወዳድረው ካሸነፋበት ናሙና ምንም ለውጥ ሳያደርጉ በራሳቸው ወጪ ጭነው የማቅረብና ደረጃውን ያልጠበቀ እቃ ከሆነ መልሰው ትክከለኛውን እቃ የማምጣት ግዴታ አለባቸው።
9. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ጽ/ቤቱ ውስጥ ሲሆን ጨረታው ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት በአል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል።
10. የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% /C.PO/ በቅድሚያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ሀ. በማንኛውም ግልፅ ጨረታ ላይ ያልታገዱ መሆን አለበት።
12. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ከቫት ጋር መሆን አለበት።
13. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ አቅራቢዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሆነ የዋስትና ደብዳቤ ካደራጀቸው አካል በጽ/ቤት ኃላፊ በኩል ተፈርሞ የቀረበ ዋስትና መሆን አለበት።
14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ልዩ ስሙ ቦሌ አራብሳ ፕሮጀክት 15 ወይም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጀርባ 200 ሜትር ገባ ብሎ።
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት