በአራዳ ከፍለ ከተማ የወረዳ 9 አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በ1ኛ ዙር ጨረታ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ልዩ ባህሪ ያላቸው የጓሮ አትክልት፣ የመስተንግዶ አገልግሎት፣ የመኪና ኪራይ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ ህትመት፣ የጉልበት ሰራተኛ፣ የኤሌክትሮኒከስ ጥገና፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ የቁሳቁስና ተገጣጣሚ ጥገና በ1ኛው ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 30, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፦ 01/2018

በአራዳ ከፍለ ከተማ የወረዳ 9 አስተዳደር /ቤት 2018 በጀት ዓመት 1 ዙር ጨረታ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ልዩ ባህሪ ያላቸው የጓሮ አትክልት፣ የመስተንግዶ አገልግሎት፣ የመኪና ኪራይ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ ህትመት፣ የጉልበት ሰራተኛ፣ የኤሌክትሮኒከስ ጥገና፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ የቁሳቁስና ተገጣጣሚ ጥገና 1ኛው ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድረን መግዛትና ማሰራት እንፈልጋለን።

በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡

1. በዘርፉ አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን ነምበር፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው።

2. የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስ /ቤት 4 ፎቅ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።

4. በተጨማሪ ተጨራቾች ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስተር ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

5. በጨረታው ላይ ያወጣናቸውን እቃዎች በሙሉ ኦርጅናል እና ጥራቱን የጠበቁ ሆነው ማቅረብ የሚችሉ

6, ተጫራቾች የጨረታ ፖስታ በሚያስገቡበት ጊዜ ለተወዳደሩበት እቃ ሳንፕል የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎችን በራሳቸው ትራንስፖርት /ቤቱ ድረስ ማምጣት የሚችሉ።

8. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ ብቻ የሚወዳደሩበትን ቫት በመጨመርና በእያንዳንዱ ገጽ ፊርማና የድርጅቱ ማህተም በማኖር በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት 10/ አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በተጠቀሰው ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀ ውሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።

9. የጨረታው ማስከበሪያ በየአንዳንዱ ሎት 5,000 /አምስት ሺህ ብር /በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ አለባቸው።

10. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸው እቃዎች አጠቃላይ ዋጋ 10 % የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከጽ/ቤቱ ጋር የግዢ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል።

11. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው ቀን የስራ ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታው አከፋፈት ላይ ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን /11ኛው/ የስራ ቀን ከጠዋቱ 430 ሰዓት በወረዳው አስተዳደር አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

12. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጫራቾች ለሳንፕል /ለናሙና/ ማቅረቢያ የሚያገለግላቸውን በተጫራቹ ድርጅት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

አድራሻ፡አራት ኪሎ ዳብር ህንጻ ፊት ለፊት ብርሃንና ሰላም አለፍ ብሎ ቡና ባንክ አጠገብ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ፋይናንስ /ቤት 4 ፎቅ

ስልክ ቁጥር፡– 0118 684 783

በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 09 አስተዳዳር ፋይናንስ /ቤት