በለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 4 የአራብሳ አፀደ ህፃናት እና የመጀ/ደ/ት/ቤት ልዩ ልዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 31, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ 

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 4 የአራብሳ አፀደ ህፃናት እና የመጀ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ግዥ ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በአንደኛ ዙር ግልጽ ጨረታ

  • ሎት 1 የደንብ ልብስ፣
  • ሎት 2 የፅህፈት/የቢሮ ዕቃዎች፣
  • ሎት 3 የህትመት ውጤቶች፣
  • ሎት 4 የጽዳት ዕቃዎች፣
  • 5ኛ የህክምና ዕቃዎች፣
  • 6ኛ የትምህርት ዕቃዎች፣
  • ሎት 7 የላብራቶሪ ዕቃዎች፣
  • 8ኛ የህንፃ መሳሪያዎች፣
  • ሎት 9 ኤሌክትሮኒከስ እድሳት፣
  • ሎት 10 የጥገና፣
  • ሎት 11 የመኪና ኪራይ፣
  • ሎት 12 ኤሌክትሮኒክስ፣
  • ሎት 13 ፈርኒቸር፣
  • ሎት 14 ልዩ ልዩ ዕቃዎች ተጫራቾች የሚከተሉትን የጨረታ መመሪያ ነጥቦች በመረዳት በጨረታ ሰነድ ላይ መግለፅ ይኖርባቸዋል።

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።

4. የተጨማሪ እሴት ታክስና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ

5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን ገንዘብ ሲፒኦ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

የሎት ቁጥር

የሎት ዝርዝር ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት

የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮ.ብር

ሎት 1

የደንብ ልብስ

50000.00

ሎት 2

የቢሮ/ጽህፈት ዕቃዎች

50000.00

ሎት 3

ህትመት

5000.00

ሎት 4

የጽዳት ዕቃዎች

50000.00

ሎት 5

የህክምና ዕቃዎች

2000.00

ሎት 6

የትምህርት ዕቃዎች

30000.00

ሎት 7

የላብራቶሪ ዕቃዎች

10000.00

ሎት 8

የህንፃ መሳሪያዎች

7,000.00

ሎት 9

ኤሌክትሮኒክስ እድሳት

2000.00

ሎት 10

የጥገና ስራ

2000.00

ሎት 11

የመኪና ኪራይ

2000.00

ሎት 12

ኤሌክትሮኒክስ

60000.00

ሎት 13

ፈርኒቸር

60000.00

ሎት 14

ልዩ ልዩ ዕቃዎች

5000.00

6. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ /ለ1 ሎት/ የማይመለስ ብር በየሎቱ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 94 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ በጥቃቅንና አነስተኛ ምርት ብቻ ከክፍያ ነፃ ካደራጃቸው አካል ደብዳቤ ከጽ/ቤቱ ኃላፊ የተፈረመ እና ለሚያመርቱት ምርት /ዕቃ/ እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ በመግዛት ጨረታውን መሳተፍ ይችላሉ።

7. ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 94 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻው በማሸግ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

8. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው ቀን 3፡30 ተዘግቶ በዚያው እለት 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል።

9. አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው እንደተገለፀላቸው የውል ማስከበሪያ 10 ሲፒኦ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።

10. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ ዕቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው፤ በተጨማሪ ማንኛውም ተወዳዳሪ ናሙና ላይ ድርጅቱን የሚገልጽ ማኅተም ሆነ ማንኛውም ምልክት ካደረገ ከጨረታው ውጭ ይሆናል።

11. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ትራንስፖርት በማጓጓዝ የመስሪያ ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በማስገባት ማስረከብ ይኖርባቸዋል።

12. ተጫራቾች ባሸነፉት ዕቃዎች ላይ መስሪያ ቤቱ 20 ፐርሰንት የመቀነስ 20 ፐርሰንት የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አራብሳ ኮንዶሚንየም ጤና ጣቢያ አጠገብ

ስልክ ቁጥር፡- 011 612 4026

በአዲስ አበባ ከተማ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 የአራብሳ አፀ/ህፃናትና የመጀ/ደ/ት/ቤት