Your cart is currently empty!
በአዲስ አበባ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መሪ የመጀመሪያ ደ/ትቤት ለ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለስራ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 31, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የግዥ ጨረታ ማሳታወቂያ
የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መሪ የመጀመሪያ ደ/ትቤት ለ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለስራ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን ማለትም
- ሎት 1 የጽህፈት ዕቃዎች፣
- ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች፣
- ሎት 3 ልዩ ልዩ ዕቃዎች፣
- ሎት 4 የደንብ ልብስ፣
- ሎት 5 ቋሚ ዕቃዎች፣
- ሎት 6 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
- ሎት 7 የህክምና ዕቃዎች፣
- ሎት 8 ኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣
- ሎት 9 የትምህርት ዕቃዎች እና
- ሎት 10 የግንባታ ጥገናዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት
ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
1. በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው።
የሎት ቁጥር የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብር
- ሎት 1 የጽህፈት ዕቃዎች —————————– ብር 17900
- ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች —————————— ብር 16800
- ሎት 3 የልዩ ልዩ ዕቃዎች—————————- ብር 10600
- ሎት 4 የደንብ ልብስ——————————— ብር 18500
- ሎት 5 ቋሚ ዕቃዎች——————————— ብር 18000
- ሎት 6 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች———————- ብር 13400
- ሎት 7 የህክምና ዕቃዎች —————————- ብር 1000
- ሎት 8 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ———————– ብር 7400
- ሎት 9 የትምህርት ዕቃዎች ————————– ብር 4600
- ሎት 10 የግንባታ ጥገናዎችን ————————- ብር 18000
6. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 05 እየቀረቡ መግዛት ይቻላል።
7. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
8. ጨረታው በአስረኛው ቀን በ10፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 10፡30 ሰዓት ይከፈታል። የጨረታው መዚጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተሰጠው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
9. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።
10 ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ ዕቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
11. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት መስሪያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ አለበት።
12. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ ስልክ፡ 011 868 1536 / 011 868 1537
- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ስሙ መሪ ገበያ 500 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መሪ የመጀመሪያ ደ/ት/ቤት