Your cart is currently empty!
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ/ደ/ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 31, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-002/2018
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ/ደ/ት/ቤት በ2018 ዓ.ም ፋ/ግ/ን/የስራ ሂደት በጨረታ ቁጥር 002/18 ዓ.ም መሰረት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለመማር ማስተማር የሚውሉ እቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1. የደንብ ልብስ |
8,000.00 |
ሎት 2. አላቂ የቢሮ እቃዎች |
10,000.00 |
ሎት 3. ህትመት |
1,000.00 |
ሎት 4. አላቂ የትምህርት እቃዎች |
9,000.00 |
ሎት 5 አላቂ የፅዳት እቃዎች |
8,000.00 |
ሎት 6. የተለያዩ መጻህፍት |
500.00 |
ሎት 7. ቋሚ የኤሌክትሮኒክ እቃዎች |
8,000.00 |
ሎት 8. ፈርኒቸር የቤትና የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች- |
5,000.00 |
ሎት 9. የተለያዩ የጉልበት ስራዎችና የጭነት ለአገልግሎት |
1,000.00 |
ሎት 10, ጀኔሬተር ኮምፒውተር ፕሪንተር እድሳትና ጥገና |
7,000.00 |
ሎት 11. ጥገና |
20,000.00 |
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን።
- በዘርፉ አግባብነት ያለው ህጋዊ የታደሰ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
- በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ በእያንዳንዱ ሎት 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ ከግዥ ክፍል መውሰድ ይቻላል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ኦርጅናል እና ኮፒ ማስገባት አለባቸው፡፡ ሰነዱ ላይ ፊርማና ክብ ማህተም መኖር አለበት።
- ተጫራቾች ከላይ በየሎቱ የተጠቀሱትን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፣
- ናሙና ለሚያስፈልጋቸው የእቃ አይነቶች ናሙና ማቅረብ፣ በናሙና በማቅረብ የሚያስቸግሩትን በፎቶ ጨረታው ከመዘጋቱ ቀደም ብለው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የእቃ አይነቶች ወይም የሚቅርበው የእቃ መግለጫ (specification) መሰረት መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ናሙናዎች በጨረታ ለተሸነፉ ተጫራቾች ተመላሽ ይሆናሉ።
- ጥቃቅን እና አነስተኛ ዕቃ አቅራቢዎች ከሚመለከተው አካል በት/ቤቱ ስም የተጻፈ ደብዳቤ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ለአሸናፊው ያሸነፈበትን እቃ ትምህርት ቤቱ የእቃ መረከቢያ ስቶር ድረስ በራሱ ትራንስፖርት በማቅረብ ማስረከብ ይኖርበታል።
- ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 11:30 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- አሸናፈው ውል ገብቶ እቃዎችን ከማስገባቱ በፊት የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ አለበት።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ት/ቤቱ አሸናፊው ድርጅት ላሸነፈባቸው እቃዎች 20/100 ብዛት ከውል በፊት የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት አለው።
- በማስታወቂያው ላይ ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ።
ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር፡-011-8-35-74-96/011-8-38-79-08
አድራሻ፡- በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ለአየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ/ደ/ት/ቤት ውስጥ አየር ጤና ታክሲ ተርሚናል ፊት ለፊት ነው።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ/ደ/ት/ቤት