Your cart is currently empty!
ዓባይ ባንክ አ.ማ በአዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ በሚገኙ ቅርንጫፎች የሚገኙ ያገለገሉ ካውንተሮች እና ኬጅ ባሉበት ሁኔታ (ሳይፈርስ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Aug 31, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የሀገር ውስጥ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ያገለገሉ ካውንተር እና ኬጅ ጨረታ ሽያጭ
ማስታወቂያ ቁጥር –ዓባይ 05 2017
ዓባይ ባንክ አ.ማ በአዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ በሚገኙ ቅርንጫፎች የሚገኙ ያገለገሉ ካውንተሮች እና ኬጅ ባሉበት ሁኔታ (ሳይፈርስ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል:: ከእንጨት ከተሰራው ካውንተር በተጨማሪ የካውንተሩ የላይኛው ክፍል (እምነበረድ) እና ኬጅ የተሰራበት አሉሚኒየም እና መስታወት በዚህ ጨረታ ተካቷል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200/ ሁለት መቶ ብር ብቻ በዓባይ ባንክ ዓብይ ቅርንጫፍ በመክፈልና ደረሰኙን በመያዝ ባምቢስ ኖክ ማደያ ፊት ለፊት በሚገኘው ዝቋላ ኮምፕሌክስ 8ኛ ፎቅ ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዲፓርትመንት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 5 ቀን 2017 ድረስ ዘወትር በስራ ስዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 2፡00- 6፡00 ከስዓት በኋላ ከ11:00 እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት 2፡00-6፡00 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱትን ያገለገለ : ካውንተር እና ኬጅ የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 5 ቀን 2017 ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ በባንኩ ዋናው መ/ቤት ባምቢስ ኖክ ማደያ ፊት ለፊት ዝቋላ ኮምፕሌክስ 8ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዲፓርትመንት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው መስከረም 5 ቀን 2017 ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 9፡00 ሰዓት በተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ከጨረታ በኋላ የሚመለስ – የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 ከማንኛውም ባንክ በተሰራ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ተ.እ.ታ (VAT) 15% ጨምሮ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115571529/ 0115549741/ በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
ዓባይ ባንክ አ.ማ
ዓባይ የታላቅነት ምንጭ!