የተስፋ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 31, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የ2018 ዓ.ም ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018

የተስፋ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች በመጀመሪያ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የሎት ቁጥር

የእቃው አይነት

ሲ.ፒ.ኦ/C.P.O

ሎት 1

አላቂ የቢሮ እቃዎች 6212

6,200.00

ሎት 2

አላቂ የፅዳት እቃዎች 6218

8,000.00

ሎት 3

የደንብ ልብስ ግዥ 6211

9,000.00

ሎት 4

አላቂ የትምህርት እቃዎች 6215

6,500.00

ሎት 5

የተለያዩ ህትመት 6213

2,000.00

ሎት 6

ለሚኒስትሪሚኒግ 6419

650.00

ሎት 7

ልዩ ልዩ የእጅ መሳሪያዎችና የሕንፃ መሳሪያዎች 6219

750.00

ሎት 8

ለቋሚ እቃዎች ግዥ 6314

5,000.00

ሎት 9

ለፕላንት ለማሽነሪና ግዥ 6313

7.500.00

ሎት 10

ለፕላንት ለማሽነሪና ለመሳሪያ የእድሳት ጥገና 6243

750.00

ሎት 11

ለህንፃ ለቁሳቁስና ለተገጣጣሚዎች እድሳትና ጥገና 6244

6.500.00

ሎት 12

የክሊኒክ እቃዎች 6214

1.000.00

ሎት 13

የባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪና ፊዚክስ እቃዎች 6215

2.500.00

ሎት 14

የአይ ሲቲ አቃዎች 6215

1.000.00

ሎት 15

ለጭነት 6255

2.500.00

ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. የአገር ውስጥ ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የአገር ውስጥ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ/ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የአገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፤ቲን ነምበር ፣ ቫት ተመዝገቢ እና የ2017 ዓ.ም በጀት አመት የታደሰ የግብር ከፋይነት መለያ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  5. ሎት 1፣2 ፤3፤4፤5፤6፣7፣8፣9፤12፤13 እና 14 የሚወዳደሩ ተጫራቾች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የእቃውን ናሙና ንብረት ከፍል ገቢ ማድረግ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት ከላይ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው የብር መጠን በባንክበተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/C.PO/ ብቻ ማቅረብ አለባቸው በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት ከሆኑ ከአደራጃቸው አካል በዘርፉ መደራጀታቸውን የሚገልጽና በጨረታ ስራ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልፅ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  7. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የሚጫረቱበትን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 /አስር/ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በት/ቤቱ ፋ/ግ/ን/አስ/ደ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 በመቅርብ መግዛት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን ያጠቃለለ እና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልቶ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒና ኦርጅናል በተስፋ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋ/ግ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት 10 የስራ ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ11ኛ ቀን 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተስፋ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አዳራሽ ቁጥር 9 ይከፈታል።
  10. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸው እቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የማስያዝና የግዢ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል።
  11. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት ከሆኑ ካደራጃቸው አካል መደራጀታቸውን የጨረታ ዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  12. ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት ሳያሟሉ በጨረታ ላይ መሳተፍ ከጨረታው ያሰርዛል።
  13. መ/ቤቱ ጠቅላላ ለጨረታው ካቀረበው ብዛት 20% ከፍና ዝቅ ብሎ የግዢ ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል።
  14. ለጨረታው የተሰጠው ዋጋ ለ60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል።
  15. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • አድራሻ፡- ሾላ ገበያ ፊት ለፊት ከንግድ ባንክ ዝቅ ብሎ
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-6-58-80-08 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የተስፋ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *