Your cart is currently empty!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የተማሪ መማሪያና የመምህር ማስተማሪያ መጻህፍት ዲቨሎፕመንት ህትመት እና ሌሎች ተያያዥ አገልግሎት እና የተማሪዎች ጠረጴዛና ወንበር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 31, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ላቀዳቸው ስራዎች በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በማወዳደር
- አ/አ/ከ/አስ/ት/ቢ/NCB-G-01/2018 የተማሪ መማሪያና የመምህር ማስተማሪያ መጻህፍት ዲቨሎፕመንት ህትመት እና ሌሎች ተያያዥ አገልግሎት ግዥ ፡እና
- አ/አ/ከ/አስ/ት/ቢ/NCB_G-02/2018 ለቅድመ መደበኛ ፣ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ጠረጴዛና ወንበር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
ጨረታውን ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዚህ በጨረታ ማስታወቂያ የተጠቀሱትን ግዥ ለማቅረብ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው፣ በጨረታ ለማሳተፍ የሚያበቃ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለእያንዳንዱ ግዥ በባንክ የተመሰከረ /CPO/ 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብቻ/ በመክፈል ከቢሯችን ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 102 በመቅረብ ሰነዱን መግዛትና ቢሮ ቁጥር 101 ሰነዱን በሶፍት ኮፒ በኢሜል ወይም በፍላሽ መውሰድ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ ፤ ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ ብሎ በመለየት በታሸገ ፖስታ በማድረግ በመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፤
- ጨረታው መስከረም 12 ቀን 2017 ዓ.ም በ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለቱ ከረፋዱ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው ቁጥር 101 ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ከ 7 ቀናት በኋላ ይመለሳል።
- የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በፅሁፍ በተገለፀ ከ7 /ሰባት/ ቀናት በኋላ እስከ 15 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የውል ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ ወዲያውኑ ወደ የመንግስት ግዥ ዳይሬከቶሬቱ መጥቶ ውል መፈረም አለበት። ይህ ባይፈጸም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
- አሸናፊው ድርጅት ውል ከፈፀመ በኋላ በውሉ መሰረት በሚሰጠው ትእዛዝ መሰረት ለአገልግሎት ለማቅረብ ምቹ ማድረግ አለበት፤
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 122 64 56
አድራሻ 6 ኪሎ ወደ ጃንሜዳ መንገድ ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፊት ለፊት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Education and Training cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx House Furniture cttx, cttx Metal and Metal Working cttx, cttx Office Furniture cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Printing and Publishing cttx, cttx Promotional Items cttx, cttx Wood and Wood Working cttx