በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የብረታ ብረትና ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ የተለያዩ የብረት ዓይነቶች (ጥሬ ዕቃዎች)፣ የምርት ግብዓቶች (አላቂ ዕቃዎች)፣ የተለያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የተለያዩ የፅህፈት ዕቃዎች፣ የሴፍቲ ዕቃዎች፣ የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች፣ ፓስቸራይዝድ ወተት መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 09, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ብ.ፋ.ኢ/ብ.ግ.ጨ/001/2018

ግዥ ፈፃሚ አካል ስምበኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የብረታ ብረትና ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ

የዕቃ ግዢው ዓይነት፡

  • ሎት 1 የተለያዩ የብረት ዓይነቶች (ጥሬ ዕቃዎች)
  • ሎት 2 የምርት ግብዓቶች (አላቂ ዕቃዎች)
  • ሎት 3 የተለያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች
  • ሎት 4 የተለያዩ የፅህፈት ዕቃዎች
  • ሎት 5 የሴፍቲ ዕቃዎች
  • ሎት 6 የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች
  • ሎት 7 ፓስቸራይዝድ ወተት

የተጫራቾች መመሪያና ግዴታዎች

1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. ተጫራቾች በወጣው ጨረታ መሠረት በዘርፉ የተሰማሩና የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት

3. ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት

4. በግብር ከፋይነት የተመዘገቡና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያላቸው

5. ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥና በግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ

6. ከጥቃቅንና አነስተኛ ማህበር የሚመጡ እንዲሁም ሌሎች ተጫራቾችን ጨምሮ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋ VAT ጨምሮ ብር 2% ከታወቀ ባንክ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ብቻ በብረታ ብረት ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች ዋጋ ሞልተው የሚያቀርቡት ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያያዞ በቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ብቻ ይሆናል፡ በዋጋ መሙያ ቅፅ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ እጅግ የተከለከለ ነው።

8. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡

9. የመወዳደሪያ ጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መካኒሳ መካነ ኢየሱስ ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሯችን በግዥ ክፍል ቢሮ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡

10. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በቀረበው ዝርዝር መሠረት በመሙላት የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በብረታ ብረት ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት በግዥ ክፍል ቢሮ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡00 እንዲሁም ከሰዓት 7፡00-10፡30 የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ፡፡

11. የጨረታ ማስገቢያ ቀንና ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

12. የጨረታ መክፈቻ ቀን በህዝብ በዓላት ቀን ከዋለ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ በዓሉ በዋለ በማግስቱ ይሆናል፡፡

13. ጨረታው ጠዋት 4፡30 ላይ ተዘግቶ 4፡45 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት ይከፈታል።

14. ጨረታውን አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መዋዋል አለበት፡፡

15. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በሚገለፀው መመሪያ መሰረት ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ሰነዶችን አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

16. የብረታ ብረትና ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በቢሮ ስልክ ቁጥር 011 834 6552 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የብረታ ብረትና ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ