Your cart is currently empty!
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ ለ2018 በጀት ዓመት ለዋና ጽ/ቤትና ለገቢ ማመንጫ ማዕከላት ለሥራ አገልግሎት ላይ የሚውሉ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ብሔራዊ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
1. የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ ለ2018 በጀት ዓመት ለዋና ጽ/ቤትና ለገቢ ማመንጫ ማዕከላት ለሥራ አገልግሎት ላይ የሚውሉ –
- ሎት 1- የእንስሳት መኖ ለማቀነባበር የሚሆን እህልና ጥራጥሬ
- ሎት 2፡– ለእንጨትና ብረታ ብረት ወርክ ሾፕ ለሥራ አገልግሎት የሚሆኑ የፋብሪካ ዉጤቶች
- ሎት3፡– ለቢሮ ሥራ አገልግሎት የሚሆን የጽህፈት መሳሪያዎች
- ሎት4፡– የዶሮ ኬጅ እድሳትና ጥገና
- ሎት5- የተለያዩ ወርክሾፕ ማሽነሪዎች እድሳትና ጥገና
- ሎት6- ለድለባ አገልግሎት የሚሆን ቁም ከብቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ማሟላት አለበት።
2. የታደሰ ንግድ ፈቃድና የንግድ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAI ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የታክስ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚኖሩት 15 የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከታች የተቀመጠዉ አድራሻ በመጠቀም ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ለሎት 1 እስከ 3 ለእያንዳንዳቸዉ የጨረታውን ማስከበሪያ 100,000(አንድ መቶ ሺህ) እና ለሎት 4፣ 5 እና ሎት 6 የጨረታውን ማስከበሪያ 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም / CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት አስራ አምስተኛ ቀን 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በአስራ ስድስተኛ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ቀኑ በህዝብ በዓላትና የእረፍት ቀን ከዋለ ቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
6. የጨረታ ውድድር ሂደት እንደተጠናቀቀ ውጤቱ በኢንተርፕራይዙ በኩል ለተወዳዳሪዎች ባስመዘገቡት አድራሻ አማካይነት ይገለጽላቸዋል።
7. ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፦ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ፖሊሲና ልማት ሕንፃ ወይም ተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በሚገኝበት ሕንፃ 1ኛ ፎቅ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር /046 212 2858/0924388128/ደውሎ መጠየቅ ይቻላሉ።
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ