Your cart is currently empty!
የሸዋሮቢት ከተማ ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በግቢው ውስጥ ያለውን DCI PIPE በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 05, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የሸዋሮቢት ከተማ ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በግቢው ውስጥ ያለውን DCI PIPE በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚሁ መሠረት መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እገልፃለን።
1. በዘመኑ የታደሠ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin number ) ያላቸው
3. የቫት ተመዝጋቢ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ1 -3 የተጠቀሡትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኦርጅናል እና ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሸ/ከ/አስ/ውኃ አገልግሎት ድርጅት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታ ሠነዱን በማይመለስ ብር 1000.00 ( አንድ ሺ ብር ) ከድርጅቱ ዘወትር በስራ ሠዓት ቢሮ ቁጥር 8 መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% ጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ)ማስያዝ አለባቸው::
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሸ/ከ//ውኃ አሎት ድርጅት ማስታወቂያው በወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ 3፡00 ሠዓት ይከፈታል። የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን የሚከፈት ይሆናል።
9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ያሸነፉትን ማንኛውንም ንብረት በራሱ ትራንስፖርት ወጭ ማጓጓዝ ይኖርባቸዋል። ጨረታውን ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ድርጅታችን ድረስ በአካል በመገኘት (በስልክ ቁጥር 033 664 0040 /09 13 51 98 98) በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የሸዋሮቢት ከተማ ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት