Your cart is currently empty!
የድሬዳዋ አጠ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት የግዥ /ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለቢሮ አላቂ እቃዎች፣ ለትምህርት አላቂ እቃዎች፣ የኤሌትሪክ ዕቃዎች፣ የእስፖርት ትጥቅና ዕቃዎች፣ ለፅዳት አላቂ ዕቃዎች፣ የጥገና እቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Melekite Dire(Sep 03, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የድሬዳዋ አጠ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት የግዥ /ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት
- ሎት 1. ለቢሮ አላቂ እቃዎች
- ሎት 2 ለትምህርት አላቂ እቃዎች
- ሎት 3 የኤሌትሪክ ዕቃዎች
- ሎት 4 የእስፖርት ትጥቅና ዕቃዎች
- ሎት 5 ለፅዳት አላቂ ዕቃዎች
- ሎት 6 የጥገና እቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1. በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የ 2018 ዓ.ም የዘመኑን ግብር የከፈሉ
2. የVAT ተመዝጋቢ የሆኑ TIN ያላቸው ከገቢዎች ባለስልጣን ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችሉ
3. ተጫራቾ ክፍልች የቀረበውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር / በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በድሬ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ————————– ዓ.ም ጀምሮ ለ 7 የሥራ ቀናት በስራ ሰዓት በት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር R-9 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዳቸውን ኦርጅናልና የሚነበቡ ኮፒ ለየብቻ በመግለጽ በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ብር
- ሎት አንድ 5000 ብር
- ሎት ሁለት 5000 ብር
- ሎት ሦስት 5000 ብር
- ሎት አራት 5000 ብር
- ሎት አምስት 5000 ብር
- ሎት ስድስት 5000 ብር በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ( CPO ) ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ መ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ለ7 የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ8ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጐ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ድ/ዳ አጠ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር R-10 ይከፈታል ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ የሥራ ቀን በዚሁ ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች ግዥን ማሸነፋቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ7 ቀን ውስጥ ውል በመግባት በ 10 ቀናት ውስጥ ት/ቤቱ ድረስ በመምጣት እቃውን ማስረከብ አለባቸው
7. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው የማቀርቡ እቃዎች የኢትዮጵያን ጥሪት ደጃዎች ኤጀንሲ ስታንዳርድ ባወጣው ዝርዝር መሠረት መሆን አለበት።
ማሳሰብያ፡-
- ማንኛውም ተጫራቾች ዋጋውንም በዚህ ዶክመንት ላይ ሞልቶ ማህተም አድርጐ——– መመለስ አለበት።
- ተጨማሪ መረጃ፡- ሞባይል 09 10 18 44 87
ሞባይል 09 15 00 97 35