የኢትዮጵያ ልማት ባንክ Stationery Crusher Plant, Diesel Generator & Wheel Loader በሐራጅ ለመሸጥ ወይም ማከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 08, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የሐራጅ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በካፒታል ዕቃ ኪራይ ንግድ ሥራ አዋጅ ቁጥር 103/1998 አንቀጽ 6 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ከተከራይ የተረከባቸውን ንብረቶች በሐራጅ ለመሸጥ ወይም ማከራየት ይፈልጋል።

የተካራዩ ስም

ሐራጅ የሚካሄድበት ቦታ

የንብረት ዝርዝር

 

ንብረቶቹ የሚገኙበት ቦታ

 

የሐራጁ መነሻ ዋጋ

 

የሐራጁ ደረጃ

 

የሐራጁ ቀንና ሰዓት

 

አቶ አዱኛ ቱሉ አብዲሳ

 

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ቅርንጫፍ

Stationery Crusher Plant, Diesel Generator & Wheel Loader

ኦሮሚያ ክልል፣ ምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ ጎቶ ጊዳ ወረዳ፣ አብደታ ቀበሌ እና ነቀምቴ ከተማ  

20,779,715.0 (ሃያ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰባ ዘጠኝ ሺህ ሰባት መቶ አስራ አምስት ብር ‘/100)

2

መስከረም 14 ቀን 2018 .ምከጠዋቱ 400 ሰዓት እስከ 600 ሰዓት

ማሳሰቢያ፡-

  1. በሐራጁ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል (ግለሰብ፣ ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማኅበራት) ከቀረጥ ነፃ የመጠቀም ተመሳሳይ መብት ያለው ከሆነ ወይም መንግስት በንብረቶቹ ላይ የሚያስከፍለውን ዮጉምሩክ ቀረጥ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ ሁሉ በሐራጁ መሳተፍ ይችላል፣
  2. ንብረቱን መግዛት /መከራየት የሚፈልግ የሐረጁ መነሻ ዋጋ ሃያ አምስት በመቶ (25%) በባንክ በተረጋገጠ የባንክ ከፍያ ማዘዣ/../ በማቅረብ በሐራጁ መሳተፍ ይችላል፣
  3. ሐራጁ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ተወካዮች በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ቅርንጫፍ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይካሄዳል፣
  4.  በሐራጁ ለተሸነፉ ተሳታፊዎች ያስያዙት የባንክ ክፍያ ማዘዣ/../ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  5. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ የሐራጁ ተሳታፊ ቀሪውን ገንዘብ 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መከፈል ይኖርበታል። በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ አጠቃሎ ገንዘቡን ካልከፈለ የሐራጅ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
  6. ንብረቱን በከፊል መከራየት የሚፈልግ የሐራጁ አሸናፊ የባንኩን የማሽነሪ ኪራይ መስፈርት በማሟላት ቢያንስ ሃያ አምስት በመቶ (25%) ቅድሚያ ያሸነፈበት ዋጋ መክፈል ይኖርበታል፣
  7. የሐራጁ አሸናፊ ንብረቱን ለመከራየት የሚፈልግ ከሆነ 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የባንኩ የማሽነሪ ኪራይ መስፈርት በማሟላት እና የሚጠበቅበትን ከፍያ አጠቃሎ በመከፈል የማሽነሪ ኪራይ ውል መፈረም ይኖርበታል። በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ ግዴታውን ካልተወጣ የሐራጅ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፣
  8.  የሐራጁ አሸናፊ ንብረቶቹን በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሽያጭ የሚገዛ ከሆነ ከቀረጥ ነፃ መብት የመጠቀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል። ከቀረጥ ነፃ የመጠቀም መብት ከሌለው በመንግስት የሚጠየቁ ማንኛውንም ቀረጥ በቅድሚያ በመክፈል ንበረቱን ይረከባል፣
  9. አስራ አምስት በመቶ/15%/ የተጨማሪ እሴት ታከስ // እና ሌሎች በሕግ የተወሰኑ ከፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል፤
  10. ስለ እያንዳንዱ ንብረት ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልከ ቁጥር 057-660-0082 ወይም 057-660-0033 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል።፡፡ ንብረቱን ለመጎበኘት የሚፈልጉም ካሉ ዲስትሪክቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል።
  11. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ሐራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ