Your cart is currently empty!
የግንቦት 20 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት በ2018 ዓ.ም ከመደበኛ እና ከውስጥ በጀት ደረጃቸውን የጠበቁ ኦሪጅናል የሆኑ አላቂ የጽህፈት መሳሪያ፣ የደንብ ልብስ፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የስፖርት ትጥቅና ዕቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን እንዲሁም ልዩ ልዩ መሳሪያዎች (የህንጻ መሳሪያዎችን) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 09, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2018
የግንቦት 20 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት በ2018 ዓ.ም ከመደበኛ እና ከውስጥ በጀት ደረጃቸውን የጠበቁ ኦሪጅናል የሆኑ
- ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያ፣
- ሎት 2 የደንብ ልብስ፣
- ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች፣
- ሎት 4 የስፖርት ትጥቅና ዕቃዎች፣
- ሎት 5 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን እንዲሁም
- ሎት 6 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች (የህንጻ መሳሪያዎችን) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ቀጥሎ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታው እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን።
1. ከመንግስት ግዥ ኤጀንሲ ወይም ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ዌብ ሳይት ላይ በዘርፉ የአቅራቢነት ምዝገባ የተመዘገቡ፣ በዘርፉ ህጋዊ የታደሰና ከሚያቀርቡት ዕቃ ወይም አገልግሎት ጋር ተዛማጅነት ያለው የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ተመዝጋቢ የሆኑና የታክስ ከፋይነት ቲን ቁጥር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት1 ብር 15,000ብር (አስራ አምስት ሺህ ብር)፣ ሎት2 ብር 15,000ብር (አስራ አምስት ሺህ ብር)፣ ሎት3 ብር 15,000ብር (አስራ አምስት ሺህ ብር) ሎት4 ብር 8,000 (ስምንት ሺህ ብር ) ሎት 5 ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) እና ሎት 6 ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር በባንክ የተረጋገጠ CPO በት/ቤቱ ስም ተሰርቶ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
3.ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 150ብር (አንድ መቶ ሀምሳ ብር) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ትችላላችሁ።
4. የጨረታ ሳጥኑ በ11 ኛው የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
5. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከት/ቤቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት መፈጸም ይኖርባቸዋል፡፡
6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡– የት/ቤቱ አድራሻ ሳሪስ ከዳማ ሆቴል ወደ ሀና በሚወስደው አስፋልት ከኮከብ ፓስታና ዱቄት ፋብሪካ ከፍ ብሎ ከአስፋልት 200 ሜትር ገባ ብሎ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡-011-419-8066/ 011-419-1505
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ የግንቦት 20 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት