Your cart is currently empty!
ብሄረ ኢትዮጵያ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በአራዳ ክፍለ ከተማ በወረዳ 7 የብሄረ ኢትዮጵያ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ 2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በ 1ኛ ዙር ለአገልግሎት የሚውሉ
- ሎት1 የደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ ስፌት፣
- ሎት 2 የቢሮ እቃዎች፣
- ሎት 3 ህትመት፣
- ሎት 4 የህክምና ዕቃዎች፣
- ሎት 5 የትምህርት ዕቃዎች፣
- ሎት 8 የጽዳት ዕቃዎች፣
- ሎት 7 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣
- ሎት 8 ትራንሰፖርት፣
- ሎት 9 ጭነት፣
- ሎት 10 በኤች አይ ቪ ዙሪያ ለሚሰጥ ስልጠና ለመስተንግዶ፣
- ሎት11 የፕላንት ማሽነሪ ዕቃዎች፣
- ሎት 12 የፕላንት ማሽነሪ ጥገና እና
- ሎት 13 ህንጻ ቁሳቁስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑ ግብር የከፈሉ በአቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተመሰከረለት (CPO) በየሎቱ 10,000 ማስያዝ ይኖርበታል።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማየትና ናሙና የሚቀርብባቸውን እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል። ናሙና መረካከቢያ በድርጅቱ ስም በተዘጋጀ ፎርም መሆን ይኖርበታል በማንኛውም ወረቀት የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።
4. ተጫራቾች የአሸነፉባቸውን ዕቃዎች ወደ ት/ቤቱ ዕቃ ግምጃ ቤትይዘው ከመምጣታቸው በፊት የሚመጡበትን ሰዓት ማሳወቅ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የአሸነፉባቸውን ዕቃዎች ኦርደር ከወሰዱ በኋላ በ 5 ቀን ውስጥ ወደ ብሄረ ኢትዮጵያ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት በማድረስ ቴክኒክ ኮሚቴው ዕቃዎቹን ከናሙናው ጋር ካመሳከሩ በኋላ ተጫራቹ ዕቃዎችን ቆጥሮ ማስረከብ ይኖርበታል።
6. በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ተቋማት ራሳቸው አምርተው ለገበያ የሚያቀርቡት እቃ ወይም ምርት ከሆነ ከተደራጁበት ተቋም የአምራችነት ህጋዊ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ተቋማት አምርተው ለገበያ የማያቀርቡ ከሆነ ለሚወዳደሩበት እንደማንኛውም ተጫራቾች ጨረታ ሰነድ መግዛትና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
8. ተጫራቾች ስርዝ ድልዝ የማይነበብ ሰነድ የዋጋ ማቅረቢያ መሙያ ተቀባይነት አይኖረውም።
9. አሸናፊ ተጫራቾች 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው።
10. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ ቫትን ጨምሮ በፖስታ ታሽጎ ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ሲሆን በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከሰላሳ ደቂቃ ቆይታ በኋላ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል።
12. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ የማይመለስ 200.00(ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
13. የንግድ ፍቃዳቸው ማቅረብ የሚችሉት የዕቃዎች በንግድ ፍቃዱ ጀርባ ላይ ያለው ዝርዝር መታየት ይኖርበታል።
14. ንግድ ፍቃዱ ከሚጋብዘው ውጪ መወዳደር አይቻልም።
15. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 1 261 037/0111 260 514 በመደወል እንዲሁም በአካል ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ፊት ለፊት በመምጣት ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ፡–
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 የብሄረ ኢትዮጵያ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር 011 1 26 10 37/011 12 60 514
ብሄረ ኢትዮጵያ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት