Your cart is currently empty!
በጉለሌ ክ/ከ የሐምሌ 19/67 ቅድመ እንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ልዩ ልዩ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 26, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018
በጉለሌ ክ/ከ የሐምሌ 19/67 ቅድመ እንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ እና በውስጥ ገቢ በጀት ልዩ ልዩ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን በ1ኛ ዙር ጨረታ ከታች የተዘረዘረውን ሎቶች አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት1. የደንብ ልብስ
- ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 3 የህትመት ስራ
- ሎት 4. የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች
- ሎት 5. የፅዳት ዕቃዎች
- ሎት 6. የህንፃ የኤሌክትሪክ የቧንቧ ዕቃዎች እና ተገጣጣሚ የጥገና እና ቀለም ቅብ ስራ
- ሎት 7 ቋሚ ዕቃዎች
- ሎት8. ማሽነሪ ጥገና እና ሰርቪስ
- ሎት9. አላቂ የህከምና ዕቃዎች
- ሎት 10. የመስተንግዶ ግዥ/ቆሎ ኩኪስ ግ/ሊትር ውሃ
- ሎት11 የመኪና ኪራይ
- ሎት12. አሮጌ የስረዓተ ትምህርት መፅሀፍት ሽያጭ።
በዚህም መሰረት በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ
አመልካቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል።
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው
- በገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር መ/ቤት የአቅራቢዎች/በዘርፉ የተሰማሩበት ዘርዝር ውስጥ የተመዘገቡ የሆነ እና የማብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- ጨረታውን ለመሳተፍ በቅድሚያ የማይመለስ ብር በሎት 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን የተቋሙ ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢፕራይዝ እሴት የሚጨምሩ ከሆነ ከአደራጃቸው ተቋም በሚፅፍላቸው ደብዳቤ ያለክፍያ ሠነድ መውሰድ ይችላሉ
- ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢፕራይዝ እሴት ለማይጨምሩበት ዕቃዎች ላይ የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ኦሪጅናል እና ፎቶኮፒ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ኢንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡የሚቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑን በግልፅ መቀመጥ አለበት።
- ተጫራቾቾች ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ከጨረታው መክፈቻ ቀን በፊት ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው እቃዎች አጠቃላይ ዋጋ በሎት 1 ብር 16,000.00 ፣ ሎት2.ብር 10,000.00 ሎት 3. ብር 3,000.00 ሎት4.ብር 5,000.00 ሎት 5.ብር 15,000.00 ሎት 6.ብር. 5,580.00 ሎት 7 ብር 10,000.00 ሉት 8. ብር 1,000.0 ሎት9. ብር 400.00 ሎት 10. ብር 1,864.78 የጨረታ ዋስትና ቢያንስ ለስድስት ወር ፀንቶ የሚቆይ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.እ እስከ ጨረታ መዝጊያው ቀን ድረስ ከዋና ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀን ድረስ የሚቆይ ሆኖ ከቀኑ 11፡30 ታሽጎ በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተቋሙ ፋይናንስ ቢሮ ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ ተጫራች ውል ከመዋዋሉ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ 10% ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለበት።
- አሸናፊው ተጫራች የተገዙትን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ተቋሙ ድረስ በማቅረብ ገቢ ማድረግ አለበት።
ማሳሰቢያ፡– መስሪያቤቱ በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተጠቀሱትን እቃዎች ካለው በጀትና (የተሻለ መንገድ ካገኘ) እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የዕቃዎን 20% የመጨመር መቀነስ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
አድራሻ፡– ጉለሌ ክፍለ ከተማ ከአዲሱ ገበያ ከፍ ብሎ ወረዳ 7 አስተዳደር ጽ/ቤት አጠገብ ሆኖ ወደ ውስጥ 50ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 011-154-69-29 ወይም 011-127-53-72 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ት/ቢሮ ስር ሐምሌ 19/67 ቅድመ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Building and Finishing Materials cttx, cttx Catering and Cafeteria Services cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Construction Machinery and Equipment cttx, cttx Education and Training cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Finishig Works cttx, cttx Food and Beverage cttx, cttx Food Items and Drinks cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx Health Care, cttx Health Related Services and Materials cttx, cttx Hospitality, cttx House Furniture cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Machinery cttx, cttx Maintenance and Repair cttx, cttx Materials cttx, cttx Medical Equipment and Supplies cttx, cttx Office Furniture cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Other Sales cttx, cttx Others cttx, cttx Pharmaceutical Products cttx, cttx Plastic Products cttx, cttx Plastic Raw Materials and Products cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Printing and Publishing cttx, cttx Promotional Items cttx, cttx Rent cttx, cttx Sales, cttx Sanitary and Ceramics cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Stationery cttx, cttx Textile, cttx Tour and Travel cttx, cttx Transportation Service cttx, cttx Vehicle cttx, cttx Warehousing, cttx Water Engineering Machinery and Equipment cttx, cttx Water Pipes and Fittings cttx, Disposals and Foreclosure cttx, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx, Medical Industry cttx, Tour and Travel cttx, Transit and Transport Service cttx