Your cart is currently empty!
በአዲስ አበባ ቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ቂሊንጦ ለስራ አገልግሎት የሚውል ልዩ ልዩ የጥገና እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 14, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ቂሊንጦ ለስራ አገልግሎት የሚውል ልዩ ልዩ የጥገና እቃዎችን ናስትሮ፤ ባለ 2.5 ኤሌክትሪክ ገመድ፤ ባለ 4 ኤሌክትሪክ ገመድ፤ ባለ 36ዋት ፍሎረሰንት አንፖል፤ ባለ 36ዋት ሆልደር፤ባለ18ዋት ሆልደር፤ ባለ18ዋት አንፖል፤ ሪዚስታንት ባለ09፤ ብሬከር ባለ25ኢንች፤ ድጂታል ቴስት ላይት፤ ቶርኖ ማጠፊያ ትልቁ፤ የመበየጃ ፒንሳ 800 አምፔር፤ የኤሌክትሮድ ፐርማነንት 2.5፤ ሚስማር ባለ 8ቁጥር፤ ሚስማር ባለ 9 ቁጥር፤ ሚስማር ባለ 10 ቁጥር፤ ሚስማር ባለ12 ቁጥር፤ የቆርቆሮ ሚስማር፤ የመጋዝ ምላጭ፤ ሩቪነቶ 1/2፤ ምጣድ ቦዲ ባለ58 ስፋት፤ የሸክላ ምጣድ ባለ 58፤ ሶኬት ተንጠልጣይ፤ ኮኔክተር150AM፤ ሲባጎ ባለ 4ሚሊ፤ የእጅ ሜትር ባለ5 ሜትር፤ ጌት ቫልቭ 1/2 ፤ ኬብል ላግ፤ 240×16፤ ሞርሴቶ፤ ብሬከር 3ፌዝ፤ ብሬከር ባለ630 አ፤ ብሬከር ባለ250 አ፤ ብሬከር ባለ400አ፤ አንክባሎ አልሙንየም ባለ2ሚሊ/ግ ስፋት 58፤ የአናፂ መዶሻ፤ አጠና ማገር ባለ ከ6-8ሚሊ ቁ ባለ8 ሜ ፤የሰጌቶ ምላጭ፤ ፒፒአር ዘንግ1/2፤ ፒፒአር ዘንግ 3/4፤ መሸጎሪያ፤ ጭራ ማጠፊያ፤ መቁረጭያ ዲስክ፤ መሞረጃ ዴስክ፤ የቧንቧ መፍቻ እና ፒፒአር መቁረጫ ከተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል፡፡
በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መመሪያና መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው የተገለፀ መሆን አለበት፡፡
2. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
3. የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
5. ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ ከአደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
6. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ስም በአካውንት ቁጥር 1000007971347 ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 25 መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን/ፋይናንሻል ሰነዶችን/በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለበት፡፡ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ በአንድ ላይ አሽጎ ያቀረበ ተወዳዳሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ውጭ ይደረጋል፡፡
8. ማንኛውም ተጫራቾች የሚያስገቡት ሰነድ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ እንዲሁም ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ በተለያዩ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሚጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ ቁጥር በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ እና በሁሉም የመጫረቻ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ስርዝ ድልዝ፣ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም፡፡
9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያስይዙት ሲፒኦ ከቴክኒክ ሰነዶች ከኦርጅናሉ ጋር በአንድ ላይ አሽገው ማቅረብ አለባቸው::
10.ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO በቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ሥም አዘጋጅተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ እንዲሁም የባንክ ዋስትና የሚያስይዙ ተጫራቾች የቆይታ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 90 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል፡፡
11. ጨረታው ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት ቂሊንጦ በሚገኘው በመ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
12. የጨረታው ዝርዝር መመሪያ በጨረታ ሰነዱ ተዘርዝሮ ቀርቧል።
13. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም፡፡ እንዲሁም ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንግድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
15. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን የዓመት በዓላት ከሆነና በተለያዩ ምክንያት ዝግ ከሆነ ጨረታው በሁለተኛው ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
አድራሻ፡– ቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር አ/አ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ
ለበለጠ መረጃ ፣– 0114 716 333 / 0118 886 089 / 011 434 8986 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
በአዲስ አበባ ቀጠሮ ማዕከል ቂሊንጦ ማረፊያ ቤት