የብርሃን ጉዞ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ትምህርት ቤት ለ2018 ዓ.ም. የተለያዩ ለትምህርት የሚውል የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ህንፃ መሳሪያ፣ የስፖርት እቃ፣ የደንብ ልብስ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የኮምፒዩተር እቃ፣ መጽሐፍት እና የቢሮ እቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 13, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001

የብርሃን ጉዞ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም የተለያዩ ለትምህርት የሚውል የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ህንፃ መሳሪያ፣ የስፖርት እቃ፣ የደንብ ልብስ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የኮምፒዩተር እቃ፣ መጽሐፍትና የቢሮ እቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ

  • በሚወዳደሩበት የስራ ዘርፍ ህጋዊ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ የእሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውንና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው
  • በኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አቅራቢነት የተመዘገበና ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ
  • የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ በcpo በእያንዳንዱ ሎት ከሚያቀርበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ 2% ማቅረብ የሚችል።
  • አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በተገለፀ በ7 ቀን ውስጥ ውል መፈፀም እና 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ cpo ማስያዝ የሚችል።

ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት በት/ቤቱ ሂሳብ ከፍል ቢሮ ቁጥር 02 የማይመለስ ብር 300/ ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሳምፕል እቃዎችን ቢሮ ቁጥር 06 ማስገባት ይችላሉ።

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት ከጠዋቱ በ 4፡30 ይከፈታል። ተጫራቾች የተጫረቱበትን ዋጋ ሰነዱ ውስጥ በተዘጋጀው ዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ ብቻ ከነቫቱ በመሙላት የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ አኑረው ፋይናንሺያል ኮፒና ኦሪጅናል ቴክኒካል ኮፒና ኦሪጅናል ለብቻ ለብቻ በድምሩ 4 ፖስታ ከላይ በተጠቀሰው መጨረሻው ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰአት ከ2፡30 እስከ 11፡00 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።

ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጨረታ እቃ /ናሙና/ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው። ያለበለዚያ ከጨረታ ውጪ ናቸው። ተጫራቾች በተመረጠው ናሙና መሰረት በ7 ቀን ውስጥ እቃዎቹ በት/ቤቱ እቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማስረከብ ይኖርባቸዋል። ፈርኒቸር፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ኮምፐዩተሮችና የህንፃ መሳሪያ ናሙና በምስል ማቅረብ ይቻላል።

ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት መወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም።

መ/ቤቱ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው

አድራሻ፡- ካዛንቺስ እንደራሴ ከፍ ብሎ ብርሃን ጎዞ አ/ህ/መ/ደ/ት/ቤት

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0118931312/0118932990

የብርሃን ጉዞ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ት/ቤት