Your cart is currently empty!
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት መስተንግዶ፣ የካፌ አገልግሎት፣ ጫኝና አውራጅ ሠራተኞች፣ የሕዝብ ትራንስፖርት ከ24 ሰው በላይ የሚጭን፣ የጭነት አይሱዚ ከ50 ኩንታል በላይ የሚጭን፣ ፒካፕ የጭነት መኪና እና የጓሮ አትክልት ዘር ለመግዛት እና ለማሠራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 13, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/2018 በጀት ዓመት
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ጥራቱን የጠበቀ ግዥ ለመፈጸም ስለፈለግን
- መስተንግዶ ፤የካፌ አገልግሎት፡- በምግብ ዝግጅት የተደራጁ መረጃ ያላቸው መሆን አለባቸው።
- ጫኝና አውራጅ ሠራተኞች፤ የሕዝብ ትራንስፖርት ከ24 ሰው በላይ የሚጭን፤ የጭነት አይሱዚ ከ50 ኩንታል በላይ የሚጭን፤ፒካፕ የጭነት መኪና እና የጓሮ አትክልት ዘር ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን አገልግሎት ግዥዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሠራት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት ቀጥሎ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢ ተጫራቾች በጨረታው እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን።
1. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የአገልግሎት ግዥ እና የሚያስገቡት እቃ ጥራታቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው።
2. በወጣው ጨረታ በዘርፍ የተሰማሩ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታደሰ ንግድፈቃድ ያላቸው።
3. የቲን ነበር ተመዝጋቢ የሆኑና የንግድ ፍቃዱና ቲን ነበሩ ተናባቢ መሆን አለበት።
4. ተጫራቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸው ቫት/ቲኦቲ/ተመዝጋቢ የሆኑ ሠነዱን ሲያስገቡ ኦርጅናልና ኮፒው በማህተም የተደገፈና የባለቤትነት ሁኔታ ግልጽ የሚያደርግ ሌላ ህጋዊ ተጨማሪ ማስረጃ ካለ በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በብር መጠን በየሎቱ እደሚከተለው በየሎቱ ማስያዝ አለባቸው
5.1 ሎት1 የቢሮ መስተንግዶ አቅርቦት 3,500 /ሲስት ሺህ አምስት መቶ ብር/
5.2 ሎት2 የካፌ አገልግሎት መስተንግዶ አቅርቦት 60,000 (ስልሳ ሺህ ብር/
5.3 ሎት3 የሕዝብ እና ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት የብር መጠን 8,000 /ስምንት ሺህ ብር/
5.4 ሎት4ጫኝና አውራጅ አገልግሎት የሚሰጥ የብር መጠን 3000 /ሶስት ሺህ ብር/
5.5 ሎት5 የጓሮ አትከልት ዘር የብር መጠን 2000(ሁለት ሺህ ብር)
በማስያዝ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለበት በአስረኛው ቀን 11:30 ላይ ታሽጎ ጨረታው በተጠናቀቀ ማግስት ወይም በአስራ አንደኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
6. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክር ተጫራቾች ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑና ለወደፊቱም በመንግሥት የእቃና የአገልግሎት ግዥ እንደማይሳተፉና ጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እንደሚወረስ ማወቅ ይኖርባቸዋል።
7. በጨረታው ከቀረቡት እቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉትን ንብረት በራሱ ትራንስፖርት ወረዳ 12 ፋይናንስ ጽ/ቤት እቃ ግምጃ ቤት ማቅረብ አለበት።
9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ያልተሟላ ከሆነ ከጨረታው ውጪ እንደሚሆኑ መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
10. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ካለ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
12. ተጫራቾች ይህ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ የማይመለስ ብር 400.00 / አራት መቶ ብር/ በመክፈል ከወረዳ 12 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከአዲሱ ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቀርቦ መግዛት ይችላሉ ሰነድም ሲያስገቡ በዚሁ 6ኛ ፎቅ ላይ ነው፤ ነገር ግን ሰነድ በነጻ የሚወስዱ ተጫራቾች የሚያጽፉት ደብዳቤ በሚወዳደሩበት ዘርፍ ላይ እሴት የሚጨምሩበት መሆኑን ተገልፃ መጻፍ አለበት።
13. ማንኛውም ሰነድ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በቀረበው የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማድረግም ይሁን ማሻሻያ ማቅረብ ወይም ከጨረታው ራሱን ማግለል አይችልም፣ይህ ሆኖ ከተገኘ በጨረታው ህግ መሰረት የሚቀጣ መሆኑን መገንዘብ ይኖርበታል።
14. ጨረታውን ሲያስገቡ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-21 69 89 15 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የወረዳ2 ፋይናንስ ጽ/ቤት ታክሲ ማዞረያው ፖሊስ ጣቢያው ጋር እንገኛለን
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ12 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት