Your cart is currently empty!
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የተለያዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ እና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 15, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 04-2018
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ
- የተለያዩ አልባሳትና ጫማዎች፣
- የኮስሞቲክስና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣
- መገናኛ እና የኮምፒውተር እቃዎች ፣
- የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣
- የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ፣
- የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎች ፣ቡና እና ሻይ፣ እንዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ እና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የሚሰጥ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ከሊራንስ) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ከላይ በተ/ቁ 1 የተገለጸው ተጫራች ማሟላት ያለበት መስፈርት ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከብር 500ሺህ በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የሚፈልግ ተጫራች ሌሎች የተዘረዘሩ መረጃዎችን ማቅረብ እንዳለ ሆኖ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አይገደድም አያስፈልግም።
- ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 የዕቃዎችን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ።
- ለግልፅ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች የሚጫረቱ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 11/2018 ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ 6፡00 የዕቃዎችን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ እየከፈሉ በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 መግዛት ይችላሉ።
- የግልፅ ጨረታው ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡45 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ይከፈታል።
- ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ ለዕቃ የሰጡትን ዋጋ 5% የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲፖዚት አካውንት ቁጥር 1000013088865 ገቢ በማድረግ እና ገቢ ያደረጉበትን የባንከ አድቫይስ ከጨረታ ሰነዱ እና ከሌሎች መረጃዎች ጋር በማያያዝ በፖስታ የተጫራቹን ስም እና አድራሻ በግልጽ በመፃፍ እስከ ጨረታው መዝጊያ ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡45 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 506 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል።
- ያስያዙት ዋስትና ለአሸናፊ ተጫራቾች ከሽያጩ የሚታሰብ ሲሆን በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች የጨረታ ውጤት ከተገለጸ በኋላ ባሉት ሶስት የስራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ይሆናል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለዕቃው ከሚሰጡት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት (15%) የሚጨመር ይሆናል።
- የሃራጅ ጨረታው ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ ተጫቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅ/ጽ/ቤቱ ይካሄዳል።
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በጨረታው ያሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ 5/አምስት/ ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ እና ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
- ከላይ በተ/ቁ 11 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ማንሳት ያልቻሉ ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘ ዋስትና ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።
- በግልፅ ጨረታ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሳጥኑ ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ፣ ማሻሻል ወይም ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ውጭ ማድረግ አይችልም።
- ለግልፅ ጨረታ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- በጨረታ የሚሸጥ ዕቃ በተቋሙ ከመወረሱ በፊት የዕቃው አስመጭ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበረ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡
- ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ የወጡ ዕቃዎችን ከቅ/ጽ/ቤቱ ሰነድ በመግዛት የወጡ ዕቃዎችን ዝርዝር በመመልከት እንዲሁም በስልክ ቁጥር 058-320-74-18/058-320-75-69 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
አድራሻ፤–በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው
ዘመን ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህርዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
cttx Catering and Cafeteria Services cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Equipment cttx, cttx Food and Beverage cttx, cttx Food Items and Drinks cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx Home Appliance and Supplies cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Other Sales cttx, cttx Personal Care Products and Services cttx, cttx Safety and Security cttx, cttx Sales, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Telecommunication Equipment cttx, cttx Textile, Disposals and Foreclosure cttx, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx