Your cart is currently empty!
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ጅማ ቅ/ጽ/ቤት የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንድላ፣ ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት ገ/ዲዴሳ ዲስትሪከት ላይ የ“Grevillea robusta ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 18, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር OFWE/GU- 06/2018
ለመጀመርያ ጊዜ የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ጅማ ቅ/ጽ/ቤት በቢያ ፎላ ዲስትሪክት ላይ የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንድላ፤ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት ገ/ዲዴሳ ዲስትሪከት ላይ የ“Grevillea robusta ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሀረርጌ ቅ/ጽ/ቤት ጃሎ ሙክታር ሀዳስ ዲስትሪክት እና ምስራቅ ወለጋ ዲስትሪክት ላይ የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም
- የግንዲላ እና የእንጨት መሰንጠቂያ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የቫት (VAT) ተመዝጋቢና “TIN number ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል/ ኦይል ሊቢያ አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 እና ጨረታው በወጣበት ጅማ ቅ/ጽ/ቤት ጅማ ከተማ፤ ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት መቱ ከተማ፤ ምስራቅ ቅ/ጽ/ቤት ጊምብ ከተማ እና ሀረርጌ ቅ/ጽ/ቤት ጭሮ ከተማ በመግዛት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታተይ ቀናት ይቆይል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፋትበት ትክክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና(Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት የምትጫረቱ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች በቅ/ጽ/ቤት የምትጫረቱ መ/ቤቱ ከሚገኝበት ከተማ በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (CPO)ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111240249 በመደወል ማጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት