የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የተለያዩ እቃዎች ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Reporter(Oct 19, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 2/2018

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ እቃዎች ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤

1. የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች፣

2. Laptop, CCTV Bullet Camera, UPS Battery, Tonner Cartirages, Cat 6 Network Cable እና ቶነሮች

3. የተለያዩ ማሽኖች፡- Air Compressor ፣ Bench Grinder፣ Hand Grinder ፣የማዳበሪያ መስፊያ ማሽን፣ ማቀዝቀዣ /ፍሪጅ/፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽን፣ የውሃ ማሞቂያ ታንከር እና ሌሎች

4. በኤሌክትሪክ የሚሠራ ሞተር ሳይክል፣

5. Submersible pump፣ Submersible Trush pump፣ Horizontal water Pump፣ የሞራ መሳቢያ ፓምኘ፣ የሸሆና ጥፍር መንቀያ፣ Servo Motor፣ እና ሌሎች

6. ኮንቴነር ጋሪ፣ የሞራ ሚዛን 200ኪግ የሚመዝን፣ የቆዳ ሚዛን እስከ 500ኪ/ግ የሚመዝን፣

7. የተለያዩ የምርትና የዕርድ መገልገያ ዕቃዎች፣ የውሻ መኖ ማሸጊያ ኘላስቲክ፣ የተለያዩ ኬሚካሎች ማንኛውም ተጫራች፡-

  • በዘርፉ ወይም በተመሳሳይ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር(TIN) የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ክሊራንስ እንዲሁም በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  • ለእያንዳንዱ የጨረታ ዓይነት የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በስራ ሰዓት ከግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3ዐ ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሠነድ ማግኘት ይችላል፣
  • የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድቦንድ/ ለሚጫረትበት የጠቅላላ ዋጋውን 2% በሲ.ፒ.ኦ፣ በባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ በድርጅቱ ደረሰኝ ማስያዝ ይኖርበታል፣
  • የጨረታ ሰነዶችና ከጨረታው ጋር ተያያዥ የሆኑ ሠነዶችን በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያው ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፣
  • ጨረታው ህዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የጨረታ ኮሚቴዎች፣ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ውስጥ ይከፈታል፡፡
  • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ዐ11466-47-05 መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት